የመጪው ዕሑድ የሰንበት ቅዳሴ ሥነ ሥርዓት በካምፐን ሺርከ

Kampen_kirke_N1  የመጪው ዕሑድ ማለትም ታህሳስ 10 ቀን 2008 ዓ/ም (20. December 2015) የሰንበት ቅዳሴ ሥነ ሥርዓት የሚካሄደው በካምፐን ሺርከ (Kampen Kirke, Bøgata 1, 0655 Oslo) መሆኑን በቅድሚያ እናስታውቃለን፡፡ 

 የሰንበት ቅዳሴን ፕሮግራም የመርሃ ግብር ገጽ ውስጥ ይመልከቱ፡፡

የ 5 ወር ተኩል የሥራ ክንውንና የሂሳብ ሪፖርት

 በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክ የሰሜን ምዕራብ አውሮፓ ሃገረ ስብከት የኦስሎ ማህደረ ስብሃት ቅድስት ልደታ ለማሪያም ቤ/ክ Abune Enthos1ባለፈው ሐምሌ 12 ቀን 2007 ዓ/ም (19. juli 2015) ከሰንበት ቅዳሴ ሥነ ሥርዓት በሁዋላ ብጹዕ አባታችን አቡነ እንጦስ የሰሜን ምዕራብ አውሮፓ ሃገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በተገኙበት ባደረገው አጠቃለይ ምልአተ ጉባዔ ቤተ ክርሰቲያኑን ለመጪው 2 ዓመታት በብቃት ሊመሩ የሚችሉ የሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባዔ አመራር አካላትን መምረጡ ይታወሳል፡፡
በዚሁም መሠረት ባለፈው ዕሑድ በተነገረው ማስታወቂያ መሠረት የቀድሞው ኮሚቴ ላለፉት 5 ወር ተኩል ያደረጉትን የሥራ ክንውንና የሂሳብ ሪፖርት በነገው ዕለት ዕሑድ ነሐሴ 10 ቀን 2007 ዓ/ም (16. august 2015) ከዕለቱ የቅዳሴ ሥነ ሥርዓት በኌላ የሚያቀርቡ መሆኑን እናስታውቃለን፡፡
 

 

ወንድማችን ሊቀ ዲያቆናት ንጉሤ በድንግትኛ አደጋ አረፉ!

Nigussie1  ወንድማችን ሊቀ ዲያቆናት ንጉሤ አገር ቤት በዕረፍት ላይ እነዳሉ በደረሰባቸው ድንገተኛ የመኪና አደጋ ሕይወታቸው አልፋለች።
በዚሁ ምክንያት የተሰማንን ጥልቅ ሃዘን ለመግለጽ ባለፈው ሰኞ ሐምሌ 27 ቀን (mandag 03. august)  ከቀኑ 16 ሰዓት ጅምሮ በካምፐን ሜኒሄት የሃዘን መግለጫ ሥነ ሥርዓት ተደርጓል። በቀጣዩም ዕሑድ ነሐሴ 3 ቀን 2007 ዓ/ም (09. august 2015) በያቆብ ሺርከ በተደረገው የሰንበት ቅዳሴ ሥነ ሥርዓት ላይ የፍትሃትና የሃዘን መግለጫ ሥነ ሥርዓት ተካሂዷል።
ሊቀ ዲያቆናት ንጉሤ ለሃይማኖታቸውና ለቤተ ክርስቲያናቸው ታታሪና ቅን አገልጋይ እንዲሁም ታዛዥና ሰው አክባሪ የነበሩ ሲሆን ይህ አገልግሎታቸውና ባህሪያቸው በሁላችንም ዘንድ ለዘላለም ሲታወስ ይኖራል።
እግዚአብሔር ነፍሳቸውን በአብርሃምና በያዕቆብ መኖሪያ ያሳርፍልን!

ታላቅ የመንፈሳዊ ጉባዔ መርሃ ግብር መምህር ምህረተአብ አሰፋ በተገኙበት በታላቅ ድምቀት ተከናወነ

DSC00597   ታላቅ መንፈሳዊ ጉባዔ ቅዳሜ ግንቦት 29 ቀን (lørdag 06. juni)  እና እንዲሁም ዕሑድ ግንቦት 30 ቀን (søndag 07.  juni) መምህር ምህረተአብ አሰፋ በስካንዲኔቪያን ለመጀመሪያ ጊዜ ባደረጉት የትምህርት መርሃ ግብርና የመዝሙር ፕሮግራም በደማቅ ሁኔታ ተከናወነ። መምህር ምህረተአብ አሰፋ በስካንዲኔቪያን ለመጀመሪያ ጊዜ ያደሩት ይህ የመንፈሳዊ የትምህርት አገልግሎት መርሃ ግብር ለመከታተል በርካታ ምዕመናንና ምዕመናት ተገኝተዋል፡፡ 

 በይበልጥ እዚህ ይመልከቱ

የጌታችንና መድሃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ በዓለ ዕርገቱ ባለፈው ቅዳሜና ዕሑድ 23. og 24. mai በሶፊንበርግ ሺርከ ተከበረ

3የእርገትን በዓል ምክንያት በማድረግ ባለፈው ቅዳሜና ዕሑድ 23. og 24. mai የኦስሎ ማህደረ ስብሃት ቅድስት ልደታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያን ልዩ ልዩ የወንጌልና የማህሌት መርሃ ግብር በሶፊንበርግ ሺርከ (Sofienberg kirke) በማዘጋጀት በዓሉ በታላቅ ድምቀት ተከብሮ አለፈ፡፡

የእመቤታችን ቅድስት ልደታ ለማሪያም ዓመታዊ ክብረ በዓል በኦስሎ

10 የዘንድሮ የእመቤታቸን የቅድስት ልደታ ለማሪያም ዓመታዊ ክብረ በዓል ለመጀመሪያ ጊዜ በኖርዌይ- ኦስሎ ከተማ በቤተ ክርስቲያናቸን በደመቀ ሁኔታ ተከብሮ ዋለ፡፡ በዚሁም መሠረት  ከሚያዚያ 30 እስከ  ግንቦት 2 ቀን ማለትም (f.o.m. 08. mai t.o.m. 10. mi) ለሦሥት ቀን የተዘጋጅው መንፈሳዊ ጉባዔ ከሃገር ቤትና ከተለያዩ የአውሮፓ ከተሞች በተጋበዙ ካህናት፣ መምህራንና መዘምራን በካምፐን ሺርከ (Bøgata 1) በደመቀና በተሳካ ሁኔታ ተከናውኗል፡፡ ቤተ ክርስቲያኑ ከተቋቋመ ሦሥት ወር ያልሞላው  ቢሆንም በእግዚአብሔር ፈቃድና በእመቤታችን ተራዳኢነት እንዲሁም በምዕመናንና ምዕመናት ያልተቆጠበ ተሰትፎ ክብረ በዓሉ ከተጠበቀው በላይ በድምቀት ተከብሮ አልፏል፡፡ 

የማህደረ ስብሃት ቅድስት ልደታ ለማሪያም ቤ/ክ በኦስሎ ምስረታ

Abune Enthos1ካቲት 8 ቀን 2007 /(15. mars 2015) ጹዕ አባታችን አቡነ እንጦስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ የሰሜን ምዕራብ አውሮፓ   ሃገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በተገኙበት በኦስሎ ሶፊንበርግ ሺርከ የቅዳሴና የቤ/ክ ምሥረታ መርሃ ግብር ተካሂዷል፡፡ በዚሁም መሠረት ሊቀ ጳጳሱ ቤተ ክርስቲያኑን ቀድሰውና ባርከው ማህደረ ስብሃት ቅድስት ልደታ ለማሪያም ቤ/ክ በኦስሎ ብለው በመሰየም ቤተ ክርሰቲያኑ እንዲቋቋም አድርገዋል፡፡ በዕለቱም በርከት ያሉ ምዕመናንና ምዕመናት የተገኙ ሲሆን ሥነ ሥርዓቱ በደመቀ ሁኔታ ተከብሮ ውሏል፡፡ 

 

የቤተ ክርስቲያናችን አባል ይሁኑ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የኦስሎ ማሕደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያም ቤ/ክ አባል ለመሆን ይመዝገቡ ዘንድ በታላቅ መንፈሳዊ አክብሮት ጥሪውን ያቀርባል።

ዝርዝሩን እዚህ ይመልከቱ

 

በሊቢያና ሳውዝ አፍሪቃ ለተሰውት ወገኖቻችን የጸሎትና ምህላ ፕሮግራም ተደረገ

images1ሚያዝያ 11 ቀን 2007 /ም በሰሜን አፍሪካ ሊቢያ በንጹሃን ወገኖቻችን ላይ ለተፈጸመው አሰቃቂ የግፍ ግድያ እንዲሁም ከዚያ በፊት በደቡብ አፍሪቃ በተመሳሳይ ሁኔታ በወገኖቻችን ላይ ለደረሰው የግፍና የበደል ጭፍጨፋ በዛሬው ዕለት በቤተ ክርስቲያናችን በጸሎት፣ በፍትሃትና በተለያዩ የሃዘን ሥነ ሥርዓቶች ታስበው እንዲውሉ ተደርገዋል፡፡ በዕለቱም ስሜትን የሚነካ ግጥም ተዘጋጅቶ የተነበበ ሲሆን በቦታው የተገኘው ሕዝብም ሃዘኑን በተለያየ መንገድ ገልጿል፡፡

 

 

Den hellige Jomfru Maria sin årlige høytid feiret for første gang i Oslo

111I den Etiopisk Ortodokse Kirke feieres fødselsdagen til Den hellige Jomfru Maria i stor begivenhet årlig den 09 mai.
Ifm. dette hadde Mahidere Sibhat Kidist Lideta Le-Mariam kirke i Oslo arrangert vellykket 3 dagers kirkelig konferanse f.o.m. fredag 08. mai t.o.m søndag 10. mai som besto av bl.a. bibelundervisning, Gudstjeneste, kirkelig sanger osv. 

Etabilering av kirken

Menigheten ble etablert i seremonien som ble holdt etter godtjeneste i sofienberg kirke søndag den 15. mars 2015 og har fått sitt navn «Den Etiopisk 730-1Ortodokse Kirke nord-vest Europa Bispedømme Kidist Lideta le-Mariam Menighet i Oslo- Norge». Dette ved tilstedsvarelse, velsignelse og godkjennelse av Abune Enthos, erkebiskop av nord- og vest Europa bispedømmet etter kirkens kanon og tradisjon.

Den Etiopisk Ortodokse Tewahedo Kirke Hellige Synode som har hovedsete i Addis Ababa, Etiopia er det enste og øverste organ og myndighet i kirkens hierarki og administrasjon. Den Hellige synode har 8 bispedømmer rundt om i verden i utenlands hvor 2 av dem befinner seg i Europa. dvs. nord- og vest Europa bispedømme med hovedsete i London og sør- og øst Europa bispedømme med hovedsete i Roma.

Bli medlem

Alle uansett nasjonalitet og hudfarge som er troende i den kristne ortodokse tewahedo tro kan bli medlem etter å ha lest, oppfattet Menighetens stiftelsesdokument og Grunnordring og levert påmeldingsskjema i utfylt stand.

Les mer

Hans Hellighet Abune Mathias holdte samtale med Norges ambassader i Etiopia

Picture_008Hans Hellighet Abune Mathias I, sjette patriark og katolikosen av Etiopia, erkebiskop av Axum og Ichege av See of Saint Taklehaimanot holdte vellyket samtale med Norges ambassader i Etiopia, Andreas Gaarder. Samtalen fant sted i patriarkens kontor.