የደብሩ ፈለገ ሕይወት የሰንበት ትምህርት ቤት ዓመታዊ በዓሉን አከበረ
እሑድ ግንቦት 27 ቀን ከሰንበት የቅዳሴ ሥነ ሥርዓት በኋላ የደብሩ ፈለገ ሕይወት የሰንበት ትምህርት ቤት ዓመታዊ ክብረ በዓሉን አክብሮ ውሏል፡፡ በዕለቱም ከተዘጋጁት መርሃ ግብሮች ውስጥ የሰንበት ት/ቤቱ ዓላማ፣ ደንብና መመሪያ የቀረበ ሲሆን በተጨማሪም የዓውደ ርዕይ፣ የሥነ ጽሑፍ፣ የትምህርታዊ ጭውውት፣ የጥያቈና መልስ እንዲሁም በሥዕል የተደገፈ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክንን ቅዱሳን መካናት፣ ቅዱሳን ንዋያት፣ ቅዱሳን መጻህፍትና፣ ቅዱሳን ሥዕላትን የሚያሳዩ ማብራሪያዎች ቀርበዋል፡፡
በዕለቱም ሰንበት ት/ቤቱን ለሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት የሚያገለግሉ የአመራር አካላት ዕጩዎችን አቅርቦ አስጸድቋል፡፡