ሃይማኖታዊ ትእይንት በኖርዌይ የኦስሎ ማህደረ ስብሃት ቅድስት ልደታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያን ቀረበ፡፡
እሁድ ግንቦት 27 ቀን 2009ዓም በኖርዌይ የኦስሎ ማህደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያን ልዩ ልዩ ሃይማኖታዊ ትእይንት ታይትተዋል፡፡
በትእይንቱ ላይ በርካታ ምእመናን በተገኙበት የቅዱሳት መፃሕፍት፣የቅዱሳን ስዕላት፣ የቅዱሳን ንዋያትና የቅዱሳን መካናት በተመለከ በስዕላዊ መግለጫና በቁሳቁስ ኣስረጅነት ቀርበዋል፡፡
ለዛሬ በቅዱሳት መፃሕፍት ላይ የቀረበን ዝግጅት እንደሚከተለው እናቀርባለን፡፡
የቅዱሳን መጽሐፍት
ቅዱሳት መጻሕፍት፡- የሚባሉት የብሉያትና ሐዲሳት፣ የመነኮሳትና ሊቃውንት፣ እንዲሁም አዋልድ መጻሕፍት ናቸው፡፡ ቅዱሳት መጻሕፍት ስንል የተመረጡ፣ የተከበሩ የተወደዱና የተመሰገኑ መጻሕፍት ማለት ነው፡፡