በመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያናት ጸሎተ ምሕላ እንዲደረግ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ መመሪያ አስተላለፈ!

ሰላም፣ ፍቅር፣ አንድነትና ደኅንነት የቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ቀዳሚ ተልእኮዎች መሆናቸውን በመግለጽ በጥቅምቱ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባዔ በተላለፈው ውሳኔ መሠረት የዘንድሮውን የነቢያት ጾም በመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያናት ጸሎተ ምሕላ እንዲደረግ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ መመሪያውን አስተላልፎአል። የአሁኑ ጸሎተ ምኅላ የሚደረገው አለመግባባት በምክክር፣ በውይይት፣ በመደማመጥ እንዲፈታ፤ መከራን በመረዳዳት እንድንሻገር፣ እንደየ ኃላፊነታችን የሚጠበቅብንን ለመወጣትና የሕዝባችንን ጥያቄ ለመመለስ እንድንችል፣ ችግራችን ሁሉ ተፈትቶ ሰላምና መረጋጋት እንዲመጣ ከሃሊው አምላክ እንዲያግዘን በአንድነት ለመጮኽ እንደሆነም ተገልጿል፡፡ ሙሉ መግለጫውን እዚህ ላይ በመጫን ያንብቡ።

ጾመ_ነቢያት!

እግዚአብሔር አምላካችን ዓለምን ለማዳን ሲል የሰውን ሥጋ መልበሱን፣ ከእናቱ ቅድስት ድንግል ማርያም ጋር ወደ ግብጽ ግብር መሰደዱን፣ በባሕረ ዮርዳኖስ መጠመቁን፣ በትምህርቱ ብርሃንነት ጨለማውን ዓለም ማብራቱን፣ ለሰው ልጆች ድኅነት ሲል ልዩ ልዩ ዓይነት መከራ መቀበሉን፣ መሰቀሉን፣ መሞቱን፣ ከሙታን ተለይቶ መነሣቱን፣ ማረጉንና ዳግም ለፍርድ የሚመጣ መኾኑን በአጠቃላይ የማዳን ሥራውን በየዘመናቱ የተነሡ ቅዱሳን ነቢያት በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝተው አስቀደመው በትንቢት ተናግረዋል፡፡ ትንቢቱ ተፈጽሞ ለመመልከትም ‹‹ኃይልህን አንሣ፤ እጅህን ላክ›› እያሉ በጾም በጸሎት ተወስነው አምላክ ሰው ኾኖ ዓለምን የሚያድንበትን ጊዜ በቀናት፣ በሳምንታት፣ በወራትና በዓመታት እያሰሉ ሲጠባበቁ ቆይተዋል፡፡ የእግዚአብሔርን ሰው መኾን ሲጠባበቁ የኖሩት የነቢያት ትንቢትና ጸሎትም በእግዚአብሔር ሰው መኾን ፍጻሜ አግኝቷል፡፡
ይህን ምሥጢር በማሰብ በየዓመቱ ከኅዳር ፲፭ ቀን ጀምሮ እስከ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ልደት ዋዜማ ድረስ እንድንጾም አባቶቻችን ሥርዓት ሠርተውልናል፡፡ ይህ ጾም፣ ከሰባቱ አጽዋማት አንዱ ሲኾን፣ በስያሜም ጾመ_ነቢያት (የነቢያት ጾም) እየተባለ ይጠራል፡፡ በዚህ በጾመ ነቢያት፣ ነቢያትም ሐዋርያትም፣ ቀደምት አባቶቻችንም ጾመው በረከት አግኝተውበታል፡፡ እኛም ምዕመናን እና ምዕመናት፣ የነቢያት፣ የሐዋርያት፣ የጻድቃንና የሰማዕታት አምላክ ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም፣ ከቅዱሳን ነቢያትና ሐዋርያት በረከት እንዲያሳትፈን በዚህ በጾመ ነቢያት ወቅት በጾም በጸሎት ተወስነን እግዚአብሔርን ልንማጸነው ይገባናል፡፡

ጾሙን ጾመ ሥርየት ፤ ጾመ መድኃኒት ያድርግል፣ ሃገራችንን ሰላም ያድርግልን፣ ሱባዔውን በሰላም፣ በጤና አስፈጽሞ ለብርሃነ ልደቱ ያድርሰን!

እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ!

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሀዶ ቤ/ክ የመስቀል በዓል በዋዜማው የደመራን ችቦ በማብራት በደመቀ ሁኔታ ይከበራል፡፡ በዓሉ የንጉስ ቆስጠንጢኖስ እናት ንግሥት እሌኒ፣ ደመራ አስደምራ በእሳት ባቀጣጠለችው ጊዜ፣ ጢሱ ወደ ላይ ከወጣ በኋላ ተመልሶ ያረፈበትን ሥፍራ አስቆፍራ ጌታችን መድሃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበትን መስቀል ማግኘቷን በማስመልከት በየዓመቱ የሚከበር ታላቅ ሃይማኖታዊና ባህላዊ በዓል ነው፡፡
የመስቀል በዓል አከባበር በተባበሩት መንግስታት የሳይንስ የትምህርትና ባህል ማዕከል (UNESCO) መዝገብ በዓለም የመጀመሪያው የማይዳሰስና የማይጨበጥ ህሊናዊና ባህላዊ ቅርስ በመሆን ተመዝግቦ ይገኛል፡፡
የዘንድሮን የደመራ በዓል ቅዳሜ መስከረም 16 ቀን 2010 ዓ/ም (26. september 2020) ተከብሮ ይውላል።

መልካም አዲስ ዓመት!

መጪው ዓመት የሰላም፣ የፍቅር፣ የአንድነትና የፍትህ ዘመን እንዲሆንልን፣ ሃገራችንንና ቤተ ከርስቲያናችንን እንዲጠብቅልን የእግዚአብሔር ቸርነት፣ የእመቤታችን የቅድስት ማርያም አማላጅነት፣ የቅዱሳን መላእክት ጥበቃና ተራዳኢነት፣ የቅዱሳን አባቶች ጸጋና በረከት ከሁላችን ጋር እንዲሆን መልካም ምኞታችንን እየገለጽን በዓሉን ዓርብ መስከረም 1 ቀን 2013 ዓ/ም ከቀኑ 1100 ሰዓት ጀምሮ በቅዳሴ፣ በዝማሬና በስብከተ ወንጌል የምናከብር ስለሆነ ምዕመናንና ምዕመናት ለኮሮና በሽታ መከላከል የወጣውን ደንብ በመከተል እየተመዘገባችሁ በቦታው ተገኝታችሁ ማክበር የምትችሉ መሆኑን የደብሩ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባዔ በማክበር ያስታውቃል።

ስለ ኢትዮጵያ ድንቅ የዘመን አቆጣጠር በጥልቀት ለመረዳት በመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ የቀረበውን ትምህርት እዚህ ላይ በመጫን ይመልከቱ ክፍል አንድ፣  ክፍል ሁለት

እንኳን ለዕመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የዕርገቷ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

ጾመ ፍልሰታ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ፷፬ ዓመት በዚች ምድር ኖራ እንደ አንድ ልጇ መሞቷን፣ መነሳቷንና ማረጓን ያዩ ዘንድ ሐዋርያት የጾሙት ጾም ነው። ጾሙን ነሐሴ ፩ ቀን ጀምረው በነሐሴ አሥራ አራት ቀን ጌታችን እመቤታችንን አምጠቶ እንድትገለጥላቸው አደረገ፤ ቀበሯትም፡፡ በነሐሴ አሥራ ስድስት ቀንም እርገቷን አከበሩ፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በቤተክርስቲያናችን የእመቤታችንን በረከት ለማግኘት ከነሐሴ ፩ ቀን እስከ ነሐሴ ፲፮ ቀን ጾመ ፍልሰታ በመባል ትጾማለች፡፡ ጾሙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በአዋጅ ከደነገገቻቸው ሰባቱ አጽዋማትም አንዱ ነው። በዚህ ወቅት ምእመናንና ምዕመናት በፆም በጸሎት ተወስነው የልጇን ቸርነት የድንግልን አማላጅነት ይማጸናሉ፡፡ ጾሙን ጾመ ደህነት፣ ጾመ በረከት፣ በንሰሀ ተመልሰን ሥጋውና ደሙን ተቀብለን ከእመቤታችን በረከት አግኝተን መንግስቱን ለመወረስ የምንዘጋጅበት ያድርግልን፡፡ በዓሉን የሰላም የደስታ ያድርግልን አሜን!

በዓሉ ቅዳሜ ነሐሴ 16 ቀን (22. august) ከዋዜማው ጀምሮ በማህሌት፣ በዝማሬ፣ በስብከትና በቅዳሴ በቤ/ክርስቲያናችን በድምቀት ተከብሮ ይውላል። ምዕመናንና ምዕመናት በቦታው ተገኝታችሁ የበረከቱ ተሳታፊ እንድትሆኑ የደብሩ የሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባዔ በማክበር ይጋብዛል።

 

እንኳን ለዘንድሮው ዓመት የደብረ ታቦር በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

የደብረ ታቦር (የቡሄ) በዓል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሀዶ ቤ/ክ ቀኖና መሰረት ከዘጠኙ አብይ በዓላት ውስጥ አንዱ ሲሆን የሚከበረውም ጌታ እየሱስ ክርስቶስ በማስተማር በነበረበት ጊዜ በደብረ ታቦር ላይ ብርሃነ መለኮቱን ክብረ መንግስቱን የገለፀበት ዕለትን ለማስታወስ ነው። ይህ በዐል በየአመቱ ነሃሴ ፲፫ (13) ቀን ይከበራል።
"ከስድስት ቀንም በኋላ ኢየሱስ ጴጥሮስንና ያዕቆብን ወንድሙንም ዮሐንስን ይዞ ወደ ረጅም ተራራ ብቻቸውን አወጣቸው። በፊታቸውም ተለወጠ፥ ፊቱም እንደ ፀሐይ በራ፥ ልብሱም እንደ ብርሃን ነጭ ሆነ። እነሆም፥ ሙሴና ኤልያስ ከእርሱ ጋር ሲነጋገሩ ታዩአቸው። ማቴ - 17:1-3
ስለ ደብረ ታቦር በዓል በይበልጥ ለመረዳት እዚህ ላይ በመጫን ይመልከቱ፡፡
የደብረታቦርንና የቡሄን ትርጉምና ግንኙነት በተመለከተ ከታሪክ መጻህፍት በይበልጥ ለመረዳት እዚህበመጫን ይመልከቱ፡፡

የታላቁ የሊቀ መላዕክት የቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ የንግስ ክብረ በዓል በታላቅ ድምቀት ተከብሮ አለፈ !

የዘንድሮ የሐምሌ ወር የሊቀ መላዕክት የቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል በቤተ ክርሥቲያናችን ከቅዳሜ ምሽት ሓምሌ 18 ቀን 2012 ዓ/ም (25. juli 2020) 23:00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ማግስቱ ዕሑድ እኩለ ቀን ድረስ በማህሌት፣ በዝማሬ፣ በስብከተ ወንጌል፣ በቅዳሴና በታቦተ ንግስ በደማቅ ሁኔታ ተከብሮ አለፈ። ቪዲዮ ክሊፕ

የታላቁ የሊቀ መላዕክት የቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ የንግስ ክብረ በዓል !

የዘንድሮ የሐምሌ ወር የሊቀ መላዕክት የቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል በቤተ ክርሥቲያናችን ከቅዳሜ ምሽት ሓምሌ 18 ቀን 2012 ዓ/ም (25. juli 2020) 23:00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ማግስቱ ዕሑድ እኩለ ቀን ድረስ በማህሌት፣ በዝማሬ፣ በስብከተ ወንጌል፣ በቅዳሴና በታቦተ ንግስ በደማቅ ሁኔታ ተከብሮ ይውላል። በዕለቱም የአገልጋይ ዲያቆን የጋብቻ ሥነ ሥርዓት ይፈጸማል። በቤተ ክርስቲያናችን ሥርዓት መሠረት ሐምሌ 19 ቀን ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ቅድስት እየሉጣንና ልጇን ቅዱስ ቂርቆስን ከዕሳት ነበልባልና ከሞት አደጋ የታደገበት ቀን የሚታሰብበትና የሚከበርበት ዕለት ነው፡፡ በኦስሎና አካባቢው የምትገኙ ምዕመናንና ምዕመናት በተጠቀሰው ቦታና ሰዓት ተገኝታችሁ በዓሉን በድምቀት በማክበር የበረከቱ ተሳታፊ እንድትሆኑ የደብሩ የሰባካ መንፈሳዊ አስተዳደር በማክበር ይጋብዛል።

እንኩዋን ለበዓለ ሃምሳ/ በዓለ ጰራቅሊጦስ በሰላም አደረሳችሁ!

ጰራቅሊጦስ ማለት በግሪክ ቋንቋ አጽናኝ ማለት ነው። ጌታችን አምላካችንና መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከማረጉ በፊት ለቅዱሳን ሐዋርያት በደበብረ ዘይት ተራራ ላይ እንዲህ ብሎ ቃል ገባቶላቸው ነበር “እነሆ አባቴ የሰጠውን ተስፋ እኔ እልክላችኋለሁ፣ እናንተ ግን ከላይ ኀይልን እስክትለብሱ ድረስ በኢየሩሳሌም ከተማ ቆዩ (ሉቃ 24፡49)። በዚሁም መሠረት ከዕርገት በኋላ በአሥረኛው ቀን እስራኤላዊያን በጽዮን ከተማ በዓለ ሰዊትን (የእሸት በዓልን) ለማክበር ተሰብስበው እያሉ እንዲሁም ሐዋርያት ደግሞ ጌታችን የነገራቸውን ተስፋ እየተጠባበቁ በዚሁ በጽዮን ከተማ በቅዱስ ማርቆስ እናት ቤት ውስጥ ተሰብስበው እንዳሉ የእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ሐዋርያት ወዳሉበት፣ በጸሎትና በምሥጋና ወደ ሚተጉበት ሥፍራ በእሳት አምሳል ወርዶ በእያንዳንዳቸው ላይ ተቀመጠባቸው፡፡ ይሄንንም ሁኔታ ተከትሎ ምስጢር ተገለጠላቸው፣ ይፈሩ የነበሩት ሐዋርያትም ወንጌልን ለማስተማር ደፋሮች ሆኑ፣ በተለያየ ቋንቋዎች እንዲናገሩ እውቀት ተሰጣቸው፤ የእግዚአብሔርንም ጸጋ ተቀበሉ (የሐዋርያት ሥራ - ምዕራፍ 2:1-4)። ከዚያ ቀን ጀምሮም በየዓመቱ ይህችን ታላቅ የቤተ ክርስቲያን የልደት ቀን በዓለ ጰራቅሊጦስ በክርስቲያኖች ዘንድ በታላቅ ደስታና ምሥጋና ይከበራል፡፡ ቤተ ክርስቲያናችንም ከምታከብራቸው ዓበይት በዓላት መካከል አንዱ በዓለ ጰራቅሊጦስ ነው፡፡ የዘንድሮው የጰራቅሊጦስ በዓል ዕሑድ ግንቦት 30 ቀን 2012 ዓ/ም (07. juni 2020) ተከብሮ ይውላል።

እንኳን ለጌታችን ለአምላካችንና ለመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ዕርገት በሰላምና በጤና አደረሳችሁ!

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ከምታከብራቸው አበይት በዓላት አንዱ ዕርገት ነው። ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሞትን ድል አድርጎ ከተነሳ በኋላ ለሐዋርያቱ በተለያየ ጊዜ እየተገለጠ ለአገልግሎት ሲያዘጋጃቸው እና ስለ እግዚአብሔር መንግሥት ምስጢር እያስተማራቸው ከቆየ በኋላ በ፵ኛው ቀን "እናንተም ለዚህ ምስክሮች ናችሁ። እነሆም፥ አባቴ የሰጠውን ተስፋ እኔ እልክላችኋለሁ፤ እናንተ ግን ከላይ ኃይል እስክትለብሱ ድረስ በኢየሩሳሌም ከተማ ቆዩ።" በማለት ነግሯቸው በሐዋርያቱ ፊት አርጓል። የሉቃስ ወንጌል - ምዕራፍ 24:48-53. የዘንድሮው የዕርገት በዓል ሓሙስ ግንቦት 20 ቀን 2012 ዓ/ም (28. mai 2020) ተከብሮ ይውላል።

የዘንድሮ የእመቤታችን ቅድስት ልደቷ ለማርያም ዓመታዊ ክብረ በዓል በደመቀ ሁኔታ ተከብሮ አለፈ!

የዘንድሮ የእመቤታችን ቅድስት ልደቷ ለማርያም ዓመታዊ ክብረ በዓል በዕለተ ቀኑ ቅዳሜ ግንቦት 1 ቀን (09. mai) በኮሮና ምክንያት ለመስብሰብ ከተፈቀደው ቁጥር ባልበለጠ መዕመናንና ምዕመናት በተገኙበት በደመቀ ሁኔታ ተከብሮ አለፈ።

እንኳን ለ2012 ዓ/ም የጌታችንና የመድሃንታችን የእየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ድኅነተ ዓለምን በመስቀል ላይ ከፈጸመ በኋላ በአካለ ሥጋ ወደ መቃብር ወረደ በአካለ ነፍስ ደግሞ ወደ ሲኦል ወረዶ በሲኦል ለነበሩ ነፍሳት ነፃነትን አወጀላቸው፡፡ መለኮት፥ በተዋሕዶ፥ ከሥጋም ከነፍስም ጋር ነበረ፡፡ በታላቅ ኃይልና ሥልጣንም ከሙታን ተለይቶ ተነሣ፡፡ “ክርስቶስ በታላቅ ኃይልና ሥልጣን ከሙታን ተለይቶ ተነሣ ዲያብሎስን አሰረው አዳምን ነጻ አወጣው ከዛሬ ጀምሮ ሰላም ሆነ” በቅዳሴ ሥነ ሥርዓት ላይ እንዲሁም ምዕመናንና ምዕመናት ሰላምታ ከመለዋወጥ አስቀድሞ ይህን ቃል በመናገር የትንሣኤውን አዋጅ ማወጅና መመስከር ይገባቸዋል፡፡
በዘመኑ የነበሩት የካሕናት አለቆች፣ ጸሃፍትና ፈሪሳዊያን ግን በድርጊታቸው ሳይጸጸቱና ሳያፍሩ የክርስቶስን ድል አድራጊነት ከመቀበልና ንሰሃ ከመግባት ይልቅ ትንሳዔውን ለመደብቅና ለመካድ በሀሰት ወሬዎች መጠቀምን መረጡ (ማቴ 28:11)።
ምዕመናንና ምዕመናት በቤተ ክርስቲያናችን በወጣው ፕሮግራም መሰረት ሚያዚያ 10 ቀን 2012 ዓ/ም (18. april 2020) ከምሽቱ 23:00 ሰዓት ጀምሮ የሚደረጉ መንፈሳዊ አገልግሎቶችን በወጣው ፕሮግራም መሰረት በቤ/ክርስቲያኑ ማሕበራዊ ሚድያ በቀጥታ ስርጭት እቤታችሁ ሆናችሁ በመከታተል የበረከቱ ተካፋዮች እንድትሆኑ የደብሩ ሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባዔ ያስታውቃል።

የሰሙነ ሕማማት አምስተኛው ቀን ዕለተ ዓርብ”ስቅለት”

ዕለተ ዓርብ እኛ የሰው ልጆች በኃጢአት ቁራኝነት እንኖርበት የነበረው የጨለማ ሕይወት ያከተመባትና ፍጹም ድኅነት ያገኘንባት ታላቅ ዕለት ናት፡፡ ዕለቱም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የዓለም ሁሉ መድኃኒት ለአዳምና ለልጆቹ ሲል በመስቀል በቀራንዮ አደባባይ ተሰቅሎ መዋሉን የምናስብበት ታላቅ ቀን ነው (ማቴ.27-35-75)፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳዉሎስ "አውቀውስ ቢሆን የክብርን ጌታ ባልሰቀሉት»(1ቆሮ.1-18)" እንዳለ ይህ ዕለት የአይሁድ ካህናት ያለበደል ያለጥፋት ንጹሕና ጻድቅ የሆነውን ጌታ የሰቀሉበት ዕለት ነው፡፡ ሕዝበ ክርስቲያን በዕለተ ዓርብ ቀኑን በሙሉ የክርስቶስን ሕማሙን፣ ስቃዩን፣ ስቅለቱንና ሞቱን በስግደትና በጸሎት ይዘክራሉ፡፡ ምዕመናንና ምዕመናት በቤተ ክርስቲያናችን በወጣው ፕሮግራም መሰረት ዓርብ ሚያዚያ 9 ቀን 2012 ዓ/ም (17. april 2020) ከጠዋቱ 09:00 ሰዓት ጀምሮ የሚደረጉ መንፈሳዊ አገልግሎቶችን በቤ/ክርስቲያኑ ማሕበራዊ ሚድያ በቀጥታ ስርጭት እቤታችሁ ሆናችሁ በመከታተል የበረከቱ ተካፋዮች እንድትሆኑ የደብሩ ሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባዔ ያስታውቃል።

እግዚአብሔር አምላክ በህማምቱ 5ኛ ቀን ዓርብ ምን አደረገልኝ? በመምሀር ዶ/ር ዘበነ ለማ በተከታታይ የሚሰጠውን ትምህርት እዚህ ላይ በመጫን ይመልከቱ

ጸሎተ ሐሙስ፣ ህጥበተ እግር

ጸሎተ ሐሙስ የዓለም መድኃኒት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋን የተዋሐደ አምላክ መኾኑን ለመግለጥና ለአርአያነት ጠላቶቹ መጥተው እስኪይዙት ድረስ ሲጸልይ ያደረበት ቀን በመሆኑ "ጸሎተ ሐሙስ" ይባላል (ማቴ. 26፥36–56)፡፡ ከሰባቱ ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን አንዱ ምሥጢረ ቍርባንም በዚህ ቀን ተመሥርቷልና ዕለቱ "የምሥጢር ቀን" ይባላል (ሉቃስ 22፥14-20)። ጌታችን በዚህ ዕለት የደቀ መዛሙርቱን እግር በፍጹም ትሕትና ዝቅ ብሎ አጥቧል (ዮሐንስ ወንጌል -13:4-17)። ይህም ኢየሱስ ክርስቶስ የዓለምን ዅሉ ኃጢአት ለማጠብ የመጣ የንጽሕና፣ የቅድስና አምላክ መኾኑን ያሳያል፡፡ ስለዚህም ዕለቱ በተጨማሪም "ሕጽበተ ሐሙስ ወይንም ሕጽበተ እግር" ይባላል፡፡ ይህን ለማስታወስ ዛሬም ሊቃነ ጳጳሳትና ቀሳውስት "የእኛን የሕዝብህን ኃጢአት እጠብ፤ እኛም የአንተን አርአያነት ተከትለን የልጆቻችንን እግር እናጥባለን" ሲሉ በቤተ ክርስቲያን የተገኙ ምእመናንን እግር በወይንና በወይራ ቅጠል ያጥባሉ፡፡
ምዕመናንና ምዕመናት በቤተ ክርስቲያናችን በወጣው ፕሮግራም መሰረት ሐሙስ ሚያዚያ 8 ቀን 2012 ዓ/ም (16. april 2020) ከጠዋቱ 09:00 ሰዓት ጀምሮ የሚደረጉ መንፈሳዊ አገልግሎቶችን በቤ/ክርስቲያኑ ማሕበራዊ ሚድያ በቀጥታ ስርጭት እቤታችሁ ሆናችሁ በመከታተል የበረከቱ ተካፋዮች እንድትሆኑ የደብሩ ሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባዔ ያስታውቃል።

እግዚአብሔር አምላክ በህማምቱ 4ኛ ቀን ሐሙስ ምን አደረገልኝ? በመምሀር ዶ/ር ዘበነ ለማ በተከታታይ የሚሰጠውን ትምህርት እዚህ ላይ በመጫን ይመልከቱ

በሕማማት ሐሙስ ለምን ይቀደሳል? ይህንን በተመለከተ በመምሀር ዶ/ር ዘበነ ለማ የተሰጠውን ትምህርት እዚህ ላይ በመጫን ይመልከቱ።

ሰሞነ ህማማት

ከሆሳዕና ጀምሮ እስከ ትንሳኤ ሌሊት ያሉት ዕለታት የሚገኙበት ሳምንት ሰሙነ ሕማማት ይባላል፡፡ ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለእኛ ሲል የተቀበለውን መከራና ፍዳ በማስታወስ ክርስቲያኖች የክርስቶስን ውለታ እያሰቡ እጅግ የሚያዝኑበት፣ የሚያለቅሱበት፣ የሚሰግዱበት፣ ከሌላው ቀናትና ጊዚያት በተለየ መልኩ አምላካቸውን የሚማፀኑበት፣ ጥዋት ማታ አምላካቸውን ደጅ የሚጠኑበት፣ ሀጢያታቸውን በቤተክርስቲያን አደባባይ ለካህኑ የሚናዘዙበት ሳምንት ነው፡፡ በዚህ ሳምንት ውስጥ ታላላቅ በዓላት ማለትም ጸሎተ ሐሙስ (ህጽበት እግር)፣ ስቅለትና ቀዳም ሥዑር ይገኙበታል። ስለሆነም ምዕመናንና ምዕመናት በቤተ ክርስቲያናችን በወጣው ፕሮግራም መሰረት በወቅቱ የሚደረጉ መንፈሳዊ አገልግሎቶችን በማሕበራዊ ሚድያ በቀጥታ ስርጭት እቤታችሁ ሆናችሁ በመከታተል የበረከቱ ተካፋዮች እንድትሆኑ የደብሩ ሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባዔ ያስታውቃል። ይህ ሰሞነ ህማማት ከአምላካችን ጋር የምንገናኝበት የንስሀ፣ የጾምና የፀሎት ጊዜ ይሁንልን አሜን!!!

ስለ ሰሞነ ህማማት በይበልጥ ለመረዳት ሙአዘ ጥበባት ዲ/ን ዳንኤል ክብረት በድህረ ገጹ ላይ የጻፈውን እዚህ ላይ በመጫን ይመልከቱ፡፡
እግዚአብሔር አምላክ በህማምቱ ምን አደረገልኝ? በመምሀር ዶ/ር ዘበነ ለማ -  ሰሙነ ህማማት 1- ሰኞ፣  2- ማክሰኞ፣ 3ኛረቡዕ፣
እንዲሁም ስለስግደት ግንዛቤ ለማግኘት በመምሀር ዶ/ር ዘበነ ለማ የተሰጠውን ትምህርት እዚህ ላይ በመጫን ይመልከቱ። 

መንፈሳዊ አገልግሎት በቀጥታ ስርጭት

በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ምዕመናንና ምዕመናት ለጊዜው በየቤታቸው በመወሰን በፀሎት እንዲተጉ በመወሰኑ ምክንያት የተወሰኑ መንፈሳዊ አገልግሎቶችን በማሕበራዊ ሚድያ በቀጥታ ስርጭት እቤታቸው ሆነው በወጣው ፕሮግራም መሰረት በመከታተል የበረከቱ ተካፋዮች እንዲሆኑ የደብሩ ሰበካ ኣስተዳደር ያስታውቃል። 

በተጨማሪም አገልግሎቱን በፍጹም ጥሞናና በክርስቲያናዊ  ሥነ ሥርዓት እንድትከታተሉ በማክበር እናስገነዝባለን።

ዝርዝር ፕሮግራሙን እዚህ ላይ በመጫን ይመልከቱ።

“ሆሳዕና” የዐብይ ጾም ስምንተኛው ሳምንት

የጌታችንና የመድሃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን የትንሣኤ በዓል ከማክበራችን በፊት ያለው ሰንበት ሆሳዕና ተብሎ ይጠራል። በዚህ ቀን ኢየሱስ ክርስቶስ በታላቅ ክብር ወደ ኢየሩሳሌም የገባበት ቀን ይዘከራል፡፡ (ማቴ.21፡1-17) በዚያ ዘመን የነበሩት ሰዎች በሆሳዕና ቀን ዘምረውና ክርስቶስን አሞግሰው፣ በስቅለተ ዓርብ ቀን ግን «ይሰቀል» ብለው አብዝተው ጮሁ፡፡ በሆሳዕና ቀን «ንጉሣችን» ብለው ዘምረው በስቅለተ-ዓርብ ቀን (ከአምስት ቀናት በኋላ) ደግሞ «ደመኛችን ነው» አሉ፤ ቀድሞ ልብሳቸውን እንዳላነጠፉለትና የተቀመጠባት አህያ እንድትራመድበት እነዳላደረጉ ሁሉ፣ በኋላ የሱን ልብስ ዕጣ ተጣጥለው ተከፋፈሉት፤ «ይንገሥ» ባሉበት አንደበት መልሰው «ይሙት»፣ «ይሰቀል» ብለው ድምጻቸውን ከፍ አድርገው ጮሁ፤ ስለ መሲሕ መምጣት ግድ ያልነበረው ጲላጦስ እንኳ እነሆ ንጉሳችሁ ቢላቸው፣ እንደውም «ከዚህ ሰው ደም ንጹህ ነኝ» ብሎ በፊታቸው እጁን ቢታጠብም በደሉ በእኛ ብቻ ሳይሆን በልጅ ልጆቻችን ላይ ይሁን ብለው በመማማል እንዲሞት አጥብቀው ለመኑ፡፡ የነዚህ ሰዎች እምነት የጸናች አልነበረችምና በዘመኑ በነበሩት የካህናት አለቆች እና መምህራን ሽንገላ ከትክክለኛው መንገዳቸው ወጡ፤ ከኢየሱስ ይልቅ በርባንን መረጡ፡፡

ስለ ኮሮና ቫይረስና የቤ/ክ አገልግሎት

በመላው ዓለም ላይ እየተዛመተ ያለውን የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ለመግታትና እንዳይስፋፋ ለማድረግ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንና እንዲሁም በሌሎች የተለያዩ የዕምነት ተቋማት ውስጥ የሚገኙ የእምነቱ ተከታዮች ለጊዜው በየቤታቸው በመወሰን ፀሎት እንዲያካሂዱና በቤተ ክርስቲያንም ሆነ በሌሎች የዕምነት ተቋማት ውስጥ የሚደረጉ ሃይማኖታዊ ስርዓቶችም በተወሰኑ ካህናት አገልግሎቱ እንዲሰጥ በማድረግ በሽታው እንዳይስፋፋ ለመከለከል ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ ነው። ከቀኖና ቤተ ክርስቲያን አኳያ ከአገልጋዮች እና ከምዕመናንና ምዕመናት ሊነሱ የሚችሉ ጥያቄዎችን በተመለከተ ቤተ መቅደስ ትዘጋለች ወይ? መቼ ትዘጋለች? ቀኖናው ምን ይላል? በሚል መምህር ዶ/ር ዘበነ ለማ ያስተማሩትን እዚህ ላይ በመጫን ያዳምጡ።

ኒቆዲሞስ – የዐብይ ጾም ሰባተኛ ሳምንት

በቤተክርስቲያናችን የበዓላት ቀኖና መሰረት ሰባተኛው የዐቢይ ጾም ሰንበት ኒቆዲሞስ ይባላል፡፡ኒቆዲሞስ ቃሉ የግሪክ ሲሆን ድል ማድረግን ወይም አሸናፊነትን ያመለክታል። ኒቆዲሞስ ፈሪሳዊ፥ ከአይሁድ አለቆችና መምህራና አንዱ ሲሆን በለሊት ወደ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ እየሄደ ሰለ ሚስጥረ ጥምቀት፣ ሚስጥረ ሥላሴ፣ ሚስጥረ ሥጋዌና ሚስጥረ ትንሳኤ ሙታን መማሩንና በተለይ ሳምንቱ ስለኒቆዲሞስ ስብእና የሚነበብበት፣ የሚተረጎምበትና የሚሰበክበት ሳምንት ነው። (ዮሐ 3 : 1- 12)
ኒቆዲሞስ መምህር ሲሆን በሥጋዊ ሕይወቱ ራሱን ዝቅ አድርጎ የተማረ የትህትና አርአያ መሆኑ፣ ልቡናውን ከፍ በማድረግ ከፈሪሳውያን ህብረት ወጥቶ በትህትና ወንጌልን ለመማር በሃይማኖት ልቡናውን ለእግዚአብሔር ቃል ማዘጋጀቱ፣ በሌሊት በመትጋትና ወደ ጌታ በመሄድ ለትጋት አብነት መሆኑ፣ አይሁድ ጌታችንን ለማሰርና ለመግደል በሚዶልቱበት ወቅት ማንንም ሳይፈራ «…ሕጋችን አስቀድሞ ከእርሱ ሳይሰማ ምንስ እንዳደረገ ሳያውቅ በሰው ይፈርዳልን?..» (ዮሐ 7-50-52) በሎ በእውነት በመመስከሩ፣ እስከ መጨረሻው በመጽናት በቀራንዮ ተግኝቶ ለክብር መብቃቱ ከኒቆዲሞስ ሕይወት ከምንማራቸው ቁም ነገሮች ውስጥ ዋነኞቹ ናቸው።

“ገብር ሔር” የዐቢይ ጾም ስድስተኛው ሳምንት

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስያሜ መሠረት የዐቢይ ጾም ስድስተኛው እሑድ ወይም ሳምንት ገብር ሔር ይባላል፡፡ ገብር ሔር ማለት ታማኝ አገልጋይ ማለት ነው፡፡ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በምሳሌ መስሎ ካስተማራቸው ትምህርቶች መካከል አንዱ የሆነው ይህ ታልቅ ትምህርት በማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 25፥14-25 እንደተገለጸው ቤተ ክርስቲያን በዚህ ሳምንት የተሰጣቸውን ጸጋ አውቀው፣ ተርድተውና ተቀብለው በታማኝነት ኃለፊነታቸውን የተወጡ መልካም አገልጋዮች በጌታቸው ፊት "...አንተ በጎ ታማኝም ባሪያ፤ በጥቂቱ ታምነሃል፥ በብዙ እሾምሃለሁ፤ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ..." በመባል መወደሳቸውና መሸለማቸው ይነገራል፣ ይወሳል፣ ይሰበካል፡፡ በአንጻሩ ደግሞ የተሰጠውን ጸጋ ሳያውቅና ሳይረዳ ቸል ብሎ ኃላፊነቱን ያልተወጣ እኩይ ሎሌ በጌታው መወቀሱና መቀጣቱ የሚነገርበት፣ የሚወሳበትና የሚሰበክበት ሳምንት ነው፡፡ 

‹‹ደብረ ዘይት›› የዓብይ ጾም አምስተኛ ሳምንት

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነትና ቀኖና መሠረት የዓብይ ጾም አምስተኛ ሳምንት ‹‹ደብረ ዘይት›› በመባል ይከበራል፡፡ ጌታችን መድሃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ በደብረ ዘይት ተራራ ላይ ለደቀ መዛሙርቱ ስለ ዓለም መጨረሻና ዳግም ምጽአቱ በሚገባ አስተምሯል (ማቴ 24 ፥ 1-36)፡፡ በመሆኑም 5ኛው የዓቢይ ጾም ሰንበት የክርስቶስ ነገረ ምጽአት የሚታሰብበትና የሚሰበክበት ዕለት ስለ ሆነ በደብረ ዘይት ተሰይሟል። የደብረ ዘይት ሰንበት ስለምጽአት የተነገረበት ከመሆኑም በላይ በዚህ ዕለት ምጽአት እንደሚሆን ይታመናል፡፡ ጌታችን በደብረ ዘይት ተራራ ላይ ተቀምጦ ሳለ ደቀ መዛሙርቱ ለብቻቸዉ ወደ እርሱ ቀርበዉ “የመምጣትህና የዓለም መጨረሻ ምልክቱ ምንድር ነዉ? አሉት።” ለመጀመሪያው ጥያቄ «ስለዚያች ቀንና ስለዚያች ሰዓት ግን ከአባት ብቻ በቀር የሰማይ መላእክትም ቢሆኑ ልጅም ቢሆን የሚያውቅ የለም» (ማቴ.24፥.36) ሲል በአጭሩ ሲመልስ ስለ ሁለተኛው ጥያቄ ማለትም ስለምልክቱ ግን በሰፊው አብራርቶ አስተምሯል። ይህን በተመለከተ መምህር ዶ/ር ዘበነ ለማ ያስተማሩትን እዚህ ላይ በመጫን ያድምጡ።

“መጻጉ” የዐቢይ ጾም 4ኛ ሳምንት

የዐቢይ ፆም አራተኛው ሳምንት መጻጉዕ ይባላል፡፡ ይህ ዕለት አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ድውያንን መፈወሱ የሚዘከርበት ሳምንት ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያናችንም በዚህ ዕለት ስለ ጌታችነ ገቢረ ተዓምራትና ስለ ድውያን ፈውስ በሰፊው ታስተምራለች። መጻጉ በቤተ ሳይዳ የጸበል መጠመቂያ ቦታ ለ38 ዓመት የአልጋ ቁራኛ ሆኖ ለመዳን በተስፋ ሲጠባበቅ የነበረ ሰው ነበር፡፡ ጌታችን መድሃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ብዙ ዘመን ተኝቶ እንደኖረ አውቆ «ልትድን ትወዳለህን?» አለው፡፡ እርሱም መጠቂያው ውስጥ የሚያኖረኝ ሰው የለኝም በማለት መልስ ሰጠ፡፡ ጌታችን የሁሉም መድኃኒት በመሆኑ ወዲያው ‹‹ተነስተህ አልጋህን ተሸክመህ ሂድ» ሲለው ድኖ አልጋውን ተሸክሞ ሄደ። የዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 5: 1-15 ። 

“ምኩራብ” የዐቢይ ጾም 3ኛ ሳምንት

የዐቢይ ጾም 3ኛ ሳምንት ስያሜ "ምኩራብ" ይባላል። "ምኩራብ" ማለትም ቀጥተኛ ፍችው ኮረብታ፣ ተራራ የሚያኸል ታላቅ ሕንጻ ማለት ሲሆን ከዚህም የተነሣ የአይሁድ ቤተ ጸሎት ምኩራብ በመባል ይታወቃል። ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በምኩራብ እየገባ ለማስተማሩና በምኩራብ የሚሸጡ የሚለውጡ ነጋዴዎችን ለማስወጣቱ፣ ቤተ መቅደሱን ለማስከበሩ መታሰቢያ ሆኖ የተሰጠ ስያሜ ነው።
"ኢየሱስም ወደ መቅደስ ገባና በመቅደስ የሚሸጡትንና የሚገዙትን ሁሉ አወጣ፥ የገንዘብ ለዋጮችንም ገበታዎች የርግብ ሻጮችንም ወንበሮች ገለበጠና። "ቤቴ የጸሎት ቤት ትባላለች ተብሎ ተጽፎአል፥ እናንተ ግን የወንበዶች ዋሻ አደረጋችኋት" አላቸው።" ማቴ 21፡12-13
ይህንን በተመለከተ በመምህር ዶ/ር ዘበነ ለማ የተሰጠውን ትምህርት እዚህ ላይ በመጫን ያዳምጡ።

የዐብይ ጾም ሁለተኛው ሰንበት “ቅድስት”

የዐቢይ ጾም ሁለተኛው ሰንበት ኢትዮያዊው የዜማ ሊቅ ቅዱስ ያሬድ እንደሰየመው "ቅድሰት" ይባላል። ቅድስት ማለት ልዩ፣ ጽኑዕ፣ ክቡር ማለት ነው፡፡ እግዚአብሔር አምላካችን በባሕርዩ ቅዱስ ነው፡፡ ስለሆነም በመልኩና በምሳሌው አክብሮ የፈጠረንን እኛም ቅዱሳን እንድንሆን ይፈለጋል፡፡ "ዳሩ ግን እኔ ቅዱስ ነኝና ቅዱሳን ሁኑ" 1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 1:15-16፡፡ ከዚህ ሰንበት ዋዜማ ጀምሮ ስለ ዕለተ ሰንበት ቅድስና ይዘመራል፣ ይሰበካል። ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንም ሰንበቱንና ሳምንቱን ስለ ቅድስና ታስተምራለች፡፡ ዘፍ 2፥3፣ ዘፀ 20፥8-11፣ ዘሌ 19፥2-3

ዘወረደ የአቢይ ጾም የመጀመሪያ ሳምንት

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በአዋጅ ከደነገገቻቸው ሰባቱ አጽዋማት አንዱ የዐቢይ ወይንም የሁዳዴ ጾም ነው። የዘንድሮ የዐቢይ ጾም ከሰኞ የካቲት 16 ቀን 2012 ዓ/ም (24.02,2020) ጀምሮ ለ55 ቀናት ይጾማል፡፡ ይህ ጌታችንና መድሃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ከተጠመቀ በኋላ በገዳም ገብቶ የጾመው የአርባ ቀንና የአርባ ሌሊት ጾም ምሳሌ ነው፡፡ በዐቢይ ጾም ውስጥ የሚገኙት 8 ሣምንታት የየራሳቸው የሆነ ስያሜና ትርጉም አላቸው። በዚሁም መሰረት የዓቢይ ጾም መግቢያ የሆነው የመጀመሪያው እሁድና ከእርሱ ጋር ተያይዞ ያለው የሚቀጥለው ሳምንት “ዘወረደ” ይባላል፡፡ ዘወረደ የምስጢረ ሥጋዌ ትምህርት ነው። ማለትም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሰማይ መውረዱን፣ ከቅድስት ድንግል ማርያም መወለዱን በፍጹም ተዋሕዶ ሰው መሆኑን የሚያመለክተው የእግዚአብሔር ቃል የሚነገርበት ስለሆነ ነው፡፡
"ከሰማይም ከወረደ በቀር ወደ ሰማይ የወጣ ማንም የለም፥ እርሱም በሰማይ የሚኖረው የሰው ልጅ ነው። የዮሐንስ ወንጌል - ምዕራፍ 3:13"

የዓብይን ፆም 8ቱ ሳምንታት ስያሜዎች በተመለከተ በመምህር ዶ/ር ዘበነ ለማ የተሰጠውን አጭር ማብራሪያ እዚህ ላይ በመጫን ይመልከቱ።
እንዲሁም የአብይን ጾም የመጀመሪያ ሳምንት ዘወረደ በተመለከተ እንዲሁ በመምህር ዶ/ር ዘበነ ለማ የተሰጠውን ትምህርት እዚህ ላይ በመጫን ያዳምጡ።

ጾመ ነነዌ

ከሰባቱ የአዋጅ አጽዋማት አንዱ ሲሆን የሚጾመውም የዐብይ ጾም ከመግባቱ 2 ሳምንት በፊት ለሦስት ቀናት ነው፡፡ ይህን ጾም የጾሟት በነነዌ ይኖሩ የነበሩ ሰዎች ናቸው፡፡ በዚያ ዘመን የነበሩ የነነዌ ሰዎች ኃጢያታቸው በዝቶ በእግዚአብሔር ስለታየ ቸርነቱና ምሕረቱ የማያልቅ አምላክ መክሮ ዘክሮ እንዲመልሳቸውና ንስሐ እንዲገቡ ነቢዩ ዮናስን ወደነነዌ ሕዝብ ላከው። ትንቢተ ዮናስ ምዕራፍ 1-4።
የነነዌ ህዝብም ማቅ ለብሰው፣ ዓመድ ነስንሰው ንሰሃ በመግባታቸው ምህረትን አግኝተዋል። ጾመ ነነዌ የእግዚአብሔርን መሐሪነትና ይቅር ባይነትን የምናስታውስበት ጾም ነው፡፡ እኛ ፍጡራን በበደልን ጊዜ እግዚአብሔር ፈጽሞ ከማጥፋት ይልቅ ምክንያት ፈልጎ እንድንድን ያደርገናል፡፡ ዮናስ ለስብከት ፈቃደኛ ባይሆን እንኳን እግዚአብሔር በተለየ ጥበቡ ውስዶ እንዲሰብክ አድርጎታል። በዚህ መሰረት የነነዌ ሰዎች የተንሳሕያን ምሳሌ ናቸው፡፡ ይህ ማለት ሰው ጥፋቱን አምኖ ንስሐ ከገባ እግዚአብሔር አምላክ ይቅር ማለቱን አይተውም፡፡
እኛ ክርስቲያኖችም ይህን በማዘከር በጾምና በጸሎት ንስሐ ብንገባ እንደ ነነዌ ሰዎች ከተቃጣው ማንኛውም መቅሰፍት እንድናለን በማለት በየዓመቱ ከዓብይ ጾም መግቢያ ሁለት ሳምንት አስቀድማ ካለችው ሰኞ ጀምሮ እስከ ረቡዕ ድረስ “ጾመ ነነዌ” በማለት እንጾመዋለን፡፡ የዘንድሮ የነነዌ ጾም ከሰኞ የካቲት 02 እስከ ረቡዕ የካቲት 04 2012 ዓ/ም ድረስ ይጾማል። እግዚኣብሔር ኣምላክ ከነነዌ ጾም ለሃገራችን ምህረት፣ በረከት፣ ሰላም፣ ፍቅርና አንድነት ያድለን  አሜን!

መምህር አካለወልድ ተሰማ በመካከላችን ተገኝተው ያስተምሩናል።

የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ የፍልስፍና መምህር የሆኑት መምህር አካለወልድ ተሰማ የጥምቀትን በዓል ከእኛ ጋር ለማሳለፍ ከኢትዮጵያ መጥተው በመካከላችን ይገኛሉ። በዚሁ መሠረት በመጪው ዕሑድ ጥር 17 ቀን (26. januar 2020) ከቅዳሴ ሥነ ሥርዓት በኋላ ጠቃሚ ትምህርቶችን ያስተምሩናል። ምዕመናንና ምዕመናት በቦታው ተገኝታችሁ የበረከቱ ተሳታፊ እንድትሆኑ የደብሩ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባዔ በማክበር ይጋብዛል።

የዘንድሮ የ2012 ዓ.ም የጥምቀት በዓል በክርስቲያንሳንድ ቅድስት ድንግል ማርያም ቤ/ክ አዘጋጅነት በጋራ በድምቀት ተከብሮ ዋለ።

የዘንድሮ የጥምቀት በዓል በኖርዌይ የሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አብያተ ክርስቲያናት ማለትም
- ታቦተ ቅድስት ልደታ ለማርያም ከኦስሎ
- ታቦተ መድኃኔአለም ከስታቫንገር
- ታቦተ ቅዱስ ሚካኤል ከበርገን
- ታቦተ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከትሮንድሔም
- እንዲሁም ታቦተ ቅድስት ድንግል ማርያም ከአዘጋጇ ከክርስቲያንሳንድ ቅድስት ድንግል ማርያም ቤ/ክ በተገኙበት ቅዳሜ ጥር 09 እና ዕሁድ ጥር 10 ቀን 2012 ዓ/ም (18. og 19. januar 2020) የከትራና የጥምቀት ዓመታዊ ክብረ በዓል በታላቅ ድምቀት ተከብሮ ዋለ። ቪዲዮ ክሊፕ

የዘንድሮ 2012 ዓ/ም የጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል

ቤዛ ኩሉ ዓለም ዮም ተወልደ (የዓለም ሁሉ ቤዛ መድኃኒት ዛሬ ተወለደ)።
የዘንድሮ የልደት በዓል ከዋዜማው ሰኞ ታህሳስ 27 ቀን 2012 ዓ/ም (06. januar 2020) ከምሽቱ 20 ሰዓት ጀምሮ  በማኅሌት፣ በዝማሬ፣ በስብከትና በቅዳሴ ሥነ ሥርዓት ይከበራል፡፡ በኦስሎና አካባቢዋ የምትገኙ ምዕመናንና ምዕመናት በተጠቀሰው ቀን፣ ቦታና ሰዓት ተገኝታችሁ በዓሉን በድምቀት ለማክበርና የበረከቱ ተሳታፊ እንድትሆኑ የደብሩ የሰባካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባዔ በማክበር ይጋብዛል።

የዘንድሮ 2012 ዓ/ም የታህሳስ ወር የታላቁ መልአክ የቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል አከባበር!

የዘንድሮ 2012 ዓ/ም የታህሳስ ወር የሊቀ መላዕክት የቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል በቤተ ክርሥቲያናችን ከዋዜማው ከቅዳሜ ታህሳስ 18 ሌሊት ጀምሮ በማህሌት፣  በዝማሬ፣ በቅዳሴና በንግሥ የሚከበር በመሆኑ በኦስሎና አካባቢዋ የምትገኙ ምዕመናንና መዕመናት በቦታና በሰዓቲ ተገኝታችሁ የበረከቱ ተሳታፊ እንድትሆኑ የደብሩ የሰባካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባዔ በማክበር ይጋብዛል።
በዓሉ በዕምነታቸው የጸኑ የቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች የነበሩ ሦሥቱ ወጣቶችን (ሰለስቱ ደቂቃን) አናንያን (ሲድራቅ) ፤ አዛርያንና (ሚሣቅ) ፤ ሚሣኤልን (አብድናጎ) ሊቀ መላዕክት ቅዱስ ገብርኤል ከዕሳት ነበልባል የታደጋቸውን ቀን ምክንያት በማድረግ የሚዘከርበት ዕለት ነው። ት/ዳንኤል 3፡1-30

የኖቤል የሰላም ሽልማትን በተመለከተ የተዘጋጀ የጋራ የሰላም የጸሎት ሥነ ሥርዓት።

የጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድን የኖቤል የሰላም ሽልማት ማሸነፍን በማስመልከት የኖርዌይ አብያተ ክርስቲያናት ማህበር ሰኞ ኅዳር 29 ቀን 2012 ዓ/ም (09. desember 2019) ከ19:00 እስከ 21:00 ሰዓት ድረስ የጋራ የሰላም የጸሎት ሥነ ሥርዓት በፊላዴልፊያ ሺርከ (Filadelfiakirken) አዘጋጅቷል።
የኖርዌይ አብያተ ክርስቲያናት ማህበር (Norges Kristne Råd) በኖርዌይ ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ የክርስትና እምነት ተከታዮችንና ቤተ ክርስቲያናትን ያቀፈ ኅብረተሰብ ሲሆን፣ ማህበሩ በየዓመቱ የኖቤል የሰላም ሽልማትን በማስመልከት ተመሳሳይ የጋራ የሰላም የጸሎት ሥነ ሥርዓትን ያዘጋጃል።

በዘንድሮው ሥነ ሥርዓት ላይ ከሚገኙት ውስጥ

  • ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤልያስ - ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን
  • ቢስኮፕ ሄልጋ ሀውላንድ በርፊሊን - ከኖርዌይ ቤተክርስቲያ
  • ዋና ፀሀፊ ኤርሃር ሄርማንሰን - ከኖርዌይ የክርስቲያን ምክር ቤት
  • ዋና ፀሀፊ ዳግ ፊን ሆይ ብሮተን- የኖርዌይ ቤተክርስቲያን የእርዳታ ድርጅት
  • የኢትዮጵያ እና የኤርትራዊያን መዘምራን
  • ኢንጉን ኡልግትሰን - ከጰንጠቆስጤ እንቅስቃሴ ፡፡

በቦታው ተገኝታችሁ የዝግጂቱ ተካፋይ እንድትሆኑ በማክበር ተጋብዛች ኋል።
ቦታ: ፊላዴልፊያ ሺርከ (Filadelfiakirken), St. Olavs Gate 24, 0166 Oslo. 

በዕለቱ የመግቢያ ፕሮግራም ላይ ከሰዓቱ 17:30 ጀምሮ የኢትዮጵያ ቡናና የቀላል ምግብ ዝግጅት ይኖራል።

 

ብፁዕ አባታችን አቡነ ናትናኤል

ብፁዕ አባታችን አቡነ ናትናኤል የምስራቅ ወለጋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል በእግዚአብሔር ቅዱስ ፈቃድ የፊታችን እሑድ ጥቅምት 2 ቀን 2012 ዓ/ም (13. oktober 2019) በቤተ ክርስቲያናችን ተገኝተው የሚባርኩን ስለሆነ ምዕመናንና ምዕመናት በተጠቀሰው ቦታና ሰዓት ተገኝታችሁ ከብፁዕነታቸው ቡራኬን ትቀበሉ ዘንድ የደብሩ መንፈሳዊ አስተዳደር ሰበካ ጉባኤ ጽ/ቤትበአክብሮት ይጋብዛል።

በዕለቱም የኖርዌይ ኣብያተ ክርስቲያናት ህብረት (Norges Kristne Råd- NKR) ዋና ሃላፊ ኤርሃርድ ሄርማንሰን (Erhard Hermansen ) ቤተ ክርስቲያናችንን ለመጎብኘት በመካከላችን የሚገኙ መሆኑን እንገልጻለን።

የማጥመቅና የፈውስ አገልግሎት በቀሲስ መንግስቱ ጥላሁን (የእናቴ ልጅ)።

ከስኞ 6. mai 2019 ዓ/ም ጀምሮ ከሰኞ እስከ ቅዳሜ በተከታታይ ዘወትር ጠዋት ከ07:00 እስከ 12:00 ሰዓት ድረስ በቤተ ክርስቲያናችን ቀሲስ መንግስቱ ጥላሁን የማጥመቅና የፈውስ አገልግሎታቸውን ያከናውናሉ።  ስለሆነ ምዕመናንና ምዕመናት በተጠቀሰው ቦታና ሰዓት በመገኘት የበረከቱ ተሳታፊ እንድትሆኑ የደብሩ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባዔ በማክበር ይጋብዛል፡፡ ከሌላ አካባቢ ለመምጣት የምትፈልጉ ምዕመናንና ምዕመናት በይበልጥ መረጃ ለማግኘት ያግኙን (Kontakt oss) ገጻችንን ይመልከቱ።

የሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባዔው ወቅታዊ የሥራ ክንውንና የሂሳብ ሪፖርት ለቤተ ክርስቲያኑ አባላት ያቀርባል።

ዕሑድ ግንቦት 25 ቀን 2011 ዓ/ም (02. juni 2019) ከሰንበት የቅዳሴ ሥነ ሥርአት በኋላ የሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባዔው ወቅታዊ የሥራ ክንውንና የሂሳብ ሪፖርት ለቤ/ክርስቲያኑ አባላት ያቀርባል፡፡ በተጨማሪም ለወደፊቱ የሰበካው መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባዔ ልዩ ልዩ የሥራ ክፍሎችንና ንዑሳን ኮሚቴዎችን በማጠናከር፣ አባላትን በማሳተፍና በዕቅድ ለመመራት የውይይት መድረክ ይኖራል ስለዚህ የቤተ ክርሥቲያኑ አባላት የሆናችሁ በሙሉ ተገኝታችሁ እንድትሳተፉና የአባልነት መብትና ግዴታችሁን እንድትወጡ የደብሩ የሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባዔ በማክበር ያስታውቃል፡፡

 

የዘንድሮ የ2011 ዓ/ም የእመቤታችን ቅድስት ልደቷ ለማርያም የልደት በዓልና ዓመታዊ ክብረ በዓል።

ዮም ፍሥሐ ኮነ በእንተ ልደታ ለማርያም፤ በእመቤታችን ልደት ምክንያት ዛሬ ደስታ ሆነ፡፡
በግንቦት 1 ቀን 5ሺ ከ5መቶ የመከራው ዘመን ሊያልቅ 15 ዓመታት ሲቀሩት ሊባኖስ በሚባል ተራራ ከፀሐይ የምታበራ ሴት ልጅ ተወለደች፡፡ ይህቺም ፍጥረት ሁሉ ማለትም ደቂቀ አዳም ሁላቸው ተስፋ ሲያደርጓትና ሲጠባበቋት የነበረች የድኅነታቸው ምልክት እመቤታችን ናት፡፡
የዘንድሮው የእመቤታችን የድንግል ማርያም የልደት ክብረ በዓል በደብራችን በማህደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያም ቤተክርስቲያን የሃገረ ስብከታችን ሊቀ ጳጳስ ብፁእ ኣቡነ ኤሊያስ፣ ኣባቶች ካህናትና መምህራነ ወንጌል በተገኙበት ግንቦት ፫ እና ፬ (11. og 12. mai 2019) በታላቅ ድምቀት ይከበራል። 
በመሆኑም በደብራችሁ በኦስሎና ኣከባቢው የምትገኙ ምዕመናን በዚህ በዓል ላይ ተገኝታችሁ የበረከቱ ተካፋይ ይሆኑ ዘንድ በልዑል እግዚአብሔር ስም ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
"እናታችን ቅደስት ድንግል ማርያም ሆይ የልደትሽ ቀን ልደታችን ነው " በዓሉን በተመለከተ በመምህር ሳሙኤል ግዛው የተሰጠውን ትምህርት እዚህ ላይ በመጫን ያዳምጡ።

ወደ ቤተ ክርስቲያኑ ለመምጣት ከ Helsfyr የአውቶቡስ ቁጥር 100 ወይንም የአውቶቡስ ቁጥር 66 ን በመያዝ በ 5 ደቂቃ ውስጥ መምጣት ይችላሉ።

የጸሎትና የሃዘን መግለጫ ሥነ ሥርዓት

የወጣት አማኑኤል ተክሌን ከዚህ ዓለም በሞት መለየት ምክንያት በማድረግና እንዲሁም በአገራችን በኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ ቁጥር ET 302 ላይ በደረሰው አደጋ ላይ ህይወታቸውን ላጡ መንገደኞች በነገው ዕለት ዕሑድ 17. mars ከቅዳሴ በኋላ ከ 11:00 ሰዓት ጀምሮ የጸሎትና የሃዘን መግለጫ ሥነ ሥርዓት የሚካሄድ መሆኑን እየገለጽን በኦስሎና አካባቢው የምትገኙ ምዕመናንና ምዕመናት በተጠቀሰው ቦታና ሰዓት በመገኘት በሥነ ሥርዓቱ ላይ እንድትካፈሉ የደብሩ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባዔ በማክበር ይጋብዛል። አድራሻ Caspar Storms vei 12, 0664 Oslo, 4. etg.

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ/ክ የእስካንዲኒቢያን ሀገረ ስብከት የመጀመሪያውን ስብሰባ አካሄደ።

በአውሮፓ አኅጉር በአዲስ መልክ ከተዋቀሩት አራት ሀገረ ስብከቶች አንዱ የሆነው የእስካንዲኒቢያን ሀገረ ስብከት ሀገረ ስብከቱን በአዲስ መዋቅር ለመዘርጋትና ለማጠናከር መጋቢት 6 እና 7 ቀን 2011 ዓ/ም (15. og 16. mars 2019) ለሁለት ቀን የቆየ ስብሰባ በሃገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤልያስ ሰብሳቢነት በስዊድን እስቶክሆልም መንበረ ጵጵስና በደብረ ሰላም መድሃኔዓለም ቤተክርስቲያን ተካሂዷል። ጉባዔው በዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ውሳኔዎችን ያሳለፈ ሲሆን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የሥራ አስፈጻሚ አባላትንም መርጦአል።
1ኛ መልአከ አሚን ቀሲስ ለማ በሱፈቃድ
2ኛ መልአከ ብርሃን አባ ገብረጊዮርጊስ ካሣዬ
3ኛ መልአከ ጽዮን አባ ሙሴ ኃይለሚካኤል
4ኛ ወ/ሮ ረቂቅ ጉልላት
5ኛ አቶ አበበ ተፈሪ
6ኛ አቶ ሰለሞን ተዘራ

የታላቁ መልዓክ የሊቀ መላኩ ቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል ዓርብ ታህሳስ 19 ቀን 2011 ዓ/ም በታላቅ ድምቀት ተከበረ፡፡

ዓርብ ታህሳስ 19 ቀን 2011 ዓ/ም የታላቁ መልዓክ የሊቀ መላኩ ቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል ከአውሮፓ የተጋበዙ ካህናት፣ ዘማሪያንና መምህራን በተገኙበት በማህሌት፣ በቅዳሴ፣ በስብከተ ወንጌል፣ የታቦተ ዑደት ሥነ ሥርዓትና በሌሎች የተለያዩ ዝግጅቶች በደመቀ ሁኔታ በካምፐን ሺርከ ተከብሮ ውሏል፡፡ 

በመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያናት ጸሎተ ምሕላ እንዲደረግ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ መመሪያ አስተላለፈ።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ከጥቅምት 11 ቀን እስከ ጥቅምት 21 ቀን 2011 ዓ.ም ድረስ የተለመደውን ዓመታዊ መደበኛ ስብሰባ ሲያካሒድ ሰንብቶ ለቤተ ክርስቲያናችንና ለሀገራችን የሚበጁ ባለ 15 ነጥቦች ማህበራዊና መንፈሳዊ ውሳኔዎችን በማሳለፍ ጉባኤውን አጠናቋል፡፡ ከእነዚህም ውስጥ በአሁኑ ጊዜ በሀገራችን ኢትዮጵያ በአንዳንድ አካባቢዎች እየታየ ያለው የሰላም እጦት ችግር በቀላሉ የሚገታ ሆኖ ካልተገኘ ወደፊት አስቸጋሪ ሁኔታዎች ሊከሰቱ ይችላሉ የሚል ሥጋት በመኖሩ እንደ ቤተ ክርስቲያናችን ቀኖናዊ ሥርዓት የወንጌል ስምሪት ተዘጋጅቶ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ትምህርተ ወንጌል ተጠናክሮ እንዲሰጥ ሆኖ ከዚህም ጋር ከኅዳር 1 እስከ ኅዳር 7 ቀን 2011 ዓ.ም. (f.o.m. 10. november t.o.m. 16. november 2018) ድረስ በመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያናት ጸሎተ ምሕላ እንዲደረግ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ መመሪያውን አስተላልፎአል።

ታላቅ የምስጋናና የአንድነት መንፈሳዊ ጉባዔ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን አባቶች መካከል የተደረገውን እርቀ ሰላምና ቅዱስ ሲኖዶስ ወደ አንድነት መመለሱን አስመልክቶ በኦስሎ መካነ ቅዱሳን ቅዱስ ገብርኤል ወአቡነ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ከዓርብ ጷጉሜ 2 እስከ ጷጉሜ 3 ቀን ድረስ የምስጋናና የአንድነት ጉባዔ ተዘጋጅቷል። በጉዔውም ላይ በኖርዌይ ውስጥ የሚገኙ ሁሉም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አብያተ ክርስቲያናት እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል። በዚሁም መሰረት ቤተክርስቲያናችን ለረጅም ዓመታት በአባቶች መካከል የነበረው አለመግባባት በእርቅና በሰላም በመጠናቀቁና ቅዱስ ሲኖዶሱም ወደቀደመው አንድነቱ በመመለሱ ምክንያት የተሰማንን ደስታ ለመግለጽና ለዚህ ያደረሰንን ልዑል እግዚአብሔር በጋራ ለማመስገን በኖርዌይ የምትገኙ ምዕመናንና መዕመናት በተጠቀሰው ቦታና ሰዓት ተገኝታችሁ ጥላቻን በመቀነስ፣ ይቅርታን በማብዛት፣ ያለንን በማካፈልና በፍቅር በመደመር  በአዲስ ብሩህ ተስፋ ቀመር የተጀመረውን የለውጥ መንፈስ ከግብ ለማድረስ በሚደረገው ሂደት ውስጥ ድጋፋችንን በመግለጽ የሚፈለግብንን አስተዋጾ እንድናደርግ የደብሩ የሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባዔ በማክበር ይጋብዛል።

መንፈሳዊ አገልግሎት

መንፈሳዊ አገልግሎት ስንል በፍቃደኝነት በተሰጠን ጸጋና ስጦታ ልዑል እግዚአብሔርን በፍጹም ልብና ትህትና ማገልገል ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ለመንፈሳዊ አገልግሎት ጊዜ መመደብ ለአምላካቸን  ያለንን ፍቅር  የምንገልጽበት አንዱ መንገድ ነው፡፡ የመንፈሳዊ አገልገሎት ዘላለማዊ ዋጋ የሚከፈለው ቃሉ በማይለወጠው በልዑል እግዚአብሔር ነው፡፡ በመሆኑም ለአገልግሎት የሚውል ጊዜ ያስደስታል፡፡ ስለዚህ ለመንፈሳዊ አገልግሎት ለሚደረግልን ጥሪ ቤተ ክርሥቲያንንና እግዚአብሔርን በምንችለው አቅም ለማገልገል ፈቃደኛነታችንን ማሳየት ይገባል፡፡ ይህንን በተመለከተ መምህራን ያስተማሩትን ትምህርት እዚህ ላይ በመጫን ይመልከቱ፡፡

Den Hellige synode har erklært bønn i hele Etiopisk tewahedo kirker og menigheter!

Den Hellige synode i den Etiopisk ortodokse tewahedo kirke erklært bønn til sin troende i hele Etiopisk tewahedo kirker og menigheter. Dette ifm. fastetiden som er oppkalt etter profetene

Fastetiden som er oppkalt etter profetene

De hellige profeter i alle tidsaldre profeterte at Gud tok på seg menneskelig kjød for å frelse verden, forvist til Egypt med sin mor jomfru Maria, ble døpt i Jordan, opplyst den mørke verden gjennom lyset av hans lære, led ulike slags trengsler for menneskehetens frelse, ble korsfestet, døde, stod opp fra de døde, fór opp og vil komme igjen til dommen. Profetene som ventet på oppfyllelsen av profetien fastet og sa "Løft din styrke, send ut din hånd."
Med dette mysteriet i tankene laget våre fedre en kirkeordinans for at vi skulle faste hvert år fra 15. november til kvelden før festen for vår Herre Jesu Kristi sin fødsel. Denne fasten er en av de syv forkynnelse Faste som vi bør forholde oss til og kalles profetenes faste. I denne fasten fastet profetene, apostlene og våre forfedre og mottok velsignelser. Vi troende bør be om at Gud engasjerer oss med velsignelsen av Jomfru Maria, de hellige profetene og apostlene.

Damera festival- gjenfinning av det sanne kors

I den Etiopisk ortodokse kirke tro og samfunn feires Meskel hvert år til minne av oppdagelsen av korset som Jesus Kristus ble korsfestet. St. Helena (kjent som dronning Eleni i Etiopia), moren til Constantin den Store, gikk et søk på det sanne korset og mislyktes til hun fikk hjelp gjennom en drøm. I tråd med drømmen gjorde hun et bål og røyken ga sin retning til stedet der korset ble begravet. Helena tente fakler for å hylle hennes suksess. Siden denne gangen feires dagen i Etiopia med religious og tradisjonell seremoni ved å tenne bål.
UNESCO har også skrevet inn ritualseremonien til Meskelfestivalen, på sin representative liste over menneskets immaterielle kulturarv.
Dagen feires lørdag 26. september.

Godt Etiopisk nyttår 2013 E.C.!

Hvert år den 11. september feires det Etiopisk nyttår. Den unike Etiopisk kalender inneholder tolv måneder, hvorav hver måned har tretti dager, i tillegg til den siste trettende måned som kalles Pagumen og som inneholder fem eller seks dager som faller hvert fjerde år.

Vi ønsker den ny året består av fred, kjærlighet, samhold og rettferdighet!

Tsome Filseta- The fast of the Assumption of St. Mary

Fastetiden, Filseta er til minne om 15 dagers fasting av Apostlene som går f.o.m. nehase 1 (7. august) og t.o.m. nahase 15 (22. august). Dette som ønske fra Apostlene om å ha sine egne førstehåndsberetning om antagelsen om Jomfu Maria. I den Etiopisk Ortodokse Tewahedo kirkens kanon er dette en av de 7 faste tider. Det er en fastetid som folk bryr seg veldig mye om, og som praktiseres veldig seriøst.

Vi feirer dagen lørdag 22. august med kirkelige ritualer og sanger, preken og Gudstjeneste. Menighetsrådet inviterer alle troende til å være med og få velsignelse.

Debre Tabor feiring (Buhe)

I den Etiopisk ortodokse tewahedo kirke, feires det hvert år 19. august Debre Tabor (Buhe) festival til minne av forvandling av Jesus da han gikk opp på fjelet- "Debre tabor" for å be med sine tre disipler Peter, Jakob og Johannes. Da dukket han opp i hans strålende prakt sammen med Moses og Elia. Denne spesielle dagen heter "Debretabor" og oppkalt etter fjellet.
"Seks dager senere tok Jesus med seg Peter, Jakob og hans bror Johannes og førte dem opp på et høyt fjell, hvor de var alene. Da ble han forvandlet for øynene på dem. Ansiktet hans skinte som solen, og klærne ble hvite som lyset. Og se, Moses og Elia viste seg for dem og snakket med ham. Matt 17: 1-3

Vi feirer dagen med kirkelig ritualer og sanger, preken og Gudstjeneste. Menighetsrådet inviterer alle troende til å være med få velsignelse.

Årlig høytid av Erkeengelen Gabriel ble feiret med stor arrangement!

Den Hellige Erkeengelen Gabriel sin årlig høytid feiret fra lørdag kveld 25. juli 2020 kl. 23:00 og ut over natten med stor og forskjellige åndelige arrangementer, bl.a. kirkelig ritualer og sanger, Gudstjeneste, preken osv. Video klipp

Årlig høytid av Erkeengelen Gabriel

Den Hellige Erkeengelen Gabriel sin årlig høytid skal feires fra lørdag kveld 25. juli 2020 kl. 23:00 og ut over natten med stor og forskjellige åndelige arrangementer, bl.a. kirkelig ritualer og sanger, Gudstjeneste, preken osv.

I den Etiopisk ortodokse tewahedo kirke feires høytiden til minne for at Erkeengelen Gabriel reddet de hellige barnet Kirkos og moren Iyeruta.

Menighetsrådet inviterer alle troende til å være med og få velsignelsen!

Pinse

På Kristi himmelfartsdag minte Jesus til disiplene om at de skulle samle seg inn i Jerusalem og vente fram til han skulle komme igjen og de skal få kraft av den Hellige Ånden. (Luk 24:49).
Ti dager etter, da disiplene var samlet i Jerusalem, falt Den Hellige Ånd på dem som tunger av ild. Da ble de alle fylt med Den hellige ånd, og de begynte å tale i andre tunger, alt ettersom Ånden gav dem å tale (Apostlenes gjerninger 2:1-4). Da er Pinse dagen til minne om at Den hellige ånd kom til Apostlene. Derfor regnes Pinse også som kirkens fødselsdag. I den Etiopisk Ortodokse Tewahedo kirke feires årets Pinsedag søndag 07. juni 2020.

Kristi himmelfartsdag

I den Etiopisk Ortodokse Tewahedo kirke feires Kristi himmelfartsdag 40 dager etter Etiopisk påske.  Årets Kristi himmelfartsdag holder til torsdag 28. mai 2020.
Jesus viste seg til disiplene ved flere anledninger etter oppstandelsen. I denne perioden var han sammen med dem, fortalte dem om Guds rike og gav dem utallige bevis. Etter disse 40 dagene samler Jesus disiplene sine og lover at Den hellige ånd skal komme til dem og gi dem kraft. "Dere er vitner om dette. Og se, jeg sender over dere det som min Far har lovet. Men dere skal bli i byen til dere blir utrustet med kraft fra det høye.» Lukas 24:48-53. Deretter blir han løftet opp i en sky og tatt opp til himmelen.

Fødselsdagen av Den Hellige Jomfru Maria feiret lørdag den, 09. mai

Fødselsdagen av vår Frue Den hellige Jomfru Maria ble feiret med kirkelige ritual, Gudstjeneste, preken, andakt og kor lørdag den, 09. mai. Dette ved tilstedeværelse av under 50 mennesker ift. retningslinjen for korona virus.

Årets høytid av Oppstandelse av vår Herre Jesus Kristus

"Kristus er oppstanden! Ja, han er sannelig oppstanden!" Dette er den tradisjonelle kristne påskehilsen som varer fra Påskemorgen gjennom pinse. Denne hilsenen er aktuelle for alle kristne, uansett språk. Påskebudskapet er virkelig et herlig budskap! Først tilgivelse og rettferdiggjørelse og så frihet fra kjødet, synden og satan! Høyt lovet være Gud og vår kjære Herre Jesus Kristus!
Men daværende yppersteprester og fariseere valgte å bruke løgn for å skjule og fornekte oppstandelsen i stedet for å angre på deres ondskap handling. Matt 28:11.
Menighetsrådet informerer om å følge med på seremonien, i følge oppsatte program, fredag 17. april fra kl. 09:00 hjemmefra på direkte sending via kirkens sosialmedia.

Langfredag- 5. dag i stille uken og korsfestelsen

"Fredagen/korsfestelsen" heter Langfredag på norsk. Langfredag markerer i kristen tradisjon dagen da Jesus Kristus døde på korset. Smerten Jesus gjennomgikk var enorm. Han ble pisket og korsfestet. Som apostelen Paulus skrev i sitt første brev til Korinterne (1 Kor 1-18), hadde de kjent hvem han var, så burde de ikke ha gjort noe slikt mot ham. Men i det, Vår Herre Jesus Kristus som en inkarnasjon av Gud og den Messias som omtales i det gamle testamente, bygger bro mellom den hellige Gud og syndige mennesker ved å bli straffet for våre synder og helbredet oss (Matteus 27:35). Det holdes dagen lang seremoni i kirken til minne for Jesus sin lidelse for våre synder. Menighetsrådet informerer om å følge med på seremonien fredag 17. april fra kl. 09:00 hjemmefra på direkte sending via kirkens sosialmedia.

“Tselote hamus” torsdagens bønn (Skjærtorsdag)

"Tselote hamus" betyr "torsdagens bønn" på norsk. Det er dagen på Skjærtorsdag i Etiopisk kalender. "Tselote hamus" er den kristne feiringen av Jesu sin siste måltid med disiplene før korsfestelsen, og dermed innføringen av nattverden Luk. 22:14-20. På denne dagen vasket vår Herre disippelens føtter med ydmykhet. Johannes 13:4-17.
Menighetsrådet informerer om å følge med på seremonien torsdag 16. april fra kl. 09:00 hjemmefra på direkte sending via kirkens sosialmedia.

Den stille uken

Den stille uken er navnet til fastetidens siste uke, uken mellom Palmesøndag og Påskedag. Det er høytidelige markeringen av Jesus sin lidelse og død. I den kristne kirke tradisjonen blir denne perioden skildret som en sørgehøytid med tilsvarende sang, andakt og preg av fastetidens enkle liturgi. I den stille uken finner vi viktige dager som Skjærtorsdag – kjent som dagen for siste måltid og at Kristus vasket disiplenes føtter – Langfredag, dagen for korsfestelsen, og Påskeaften da Kristus hvilte i graven. Men natten til påskedag bryter gleden løs ved oppstandelsen fra døden.
Selv om det er vanlig å gå til kirken i den stille uken, forholder vi oss til programmet som er utgitt og følger med på seremonien hjemmefra direkte via sosialmedia.

Direkte sending av en del av Gudstjenester

I det folk holder seg hjemme pga. koronaviruset informerer Menighetsrådet om at folk kan følge med på deler av Gudstjenesten via sosiale medier i henhold til oppsatt program. Klikk her for å se på programmet.

Vi minner om folk følger programmet i ro og orden som i den kristine etikk

“Hosainna” 8. uke i fastetiden (Palmesøndag i Etiopisk kalender)

Hosainna (Palmesøndag) er, i kristen tradisjon, feiringen av Jesu inntog i Jerusalem søndagen før korsfestelsen og oppstandelsen. Ridende på et esel ble Jesus hyllet som en konge, og folk strødde palmegrener på veien til ære for ham. (Matt 21:1-17) Dette endret seg fort, og etter 5 dager ble Jesus anklaget og korsfestet for å sone verdens synd og vinne seg et hellig folk. Selv om han flere ganger har sagt til disiplene at han vil lide og dø i Jerusalem, var han likevel på vei til byen. Det skjedde for at alt det profetene har skrevet om Menneskesønnen, skulle gå i oppfyllelse.

Korona virus og kirkelige tjenester

I et forsøk på å dempe spredningen av korona virus-epidemien rundt om i verden, har den Etiopisk ortodokse tewahedo kirke og andre religiøse institusjoner begrenset deltagelse av seremonien av Gudstjenester til kun presteskapet. Medlemmer av vår kirke skal holde seg hjemme i bønn som andre trossamfunn for å forhindre sykdommen.

“Nikodemus” 7. uke i fastetiden

I den Etiopisk ortodokse tewahedo kirke oppnevnt den 7. uken i fastetiden som "Nikodemus", det greske ordet for "seier". Nikodemus var fariseer og en av jødenes rådsherrer. Han var tiltrukket av Vår Herre, men våget ikke å besøke ham åpenlyst. Han pleier å komme til Vår Herre Jesus Kristus om natten og lærer bl.a. om Dåpens sakrament, Den Hellige Treenighet, mysteriet om inkarnasjonen og Oppstandelsens mysterium. Johannes 3:1-12. Denne uken læres det i vår kirke stort sett om Nikodemus sin personlighet. Nikodemus viste at han var ydmyk, hadde innsikt og var klar over sitt åndelige behov. Han var også modig vitner. Da fariseerne skulle arrestere Vår Herre forsvarte han med å si «Loven vår dømmer vel ikke et menneske uten forhør, før en har fått vite hva det har gjort?» Johannes 7-50-52

“Gebrher” den 6. uken i fastetiden

I den Etiopisk ortodokse tewahedo kirke blir den sjette søndagen i fastetiden kalt «Gebrher» som betyr «trofast tjener». En av de mange læringene som Vår Herre og Frelser Jesus Kristus lærte oss gjennom eksempler er det som står i Mattew 25:14-25. Denne uken læres det i vår kirke om gode og trofaste tjenere som blir rost og æret for deres tillit, mens på den andre siden at den som er motvillig og dårlig tjener anklaget og straffet av Herren.

“Debre Zeit” 5. uke i fastetiden til minne for Vår Herre Jesus Kristus gjenkomst

"Debre Zeit", oljeberget på norsk, er fjellet hvor vår herre Jesus Kristus lærte disiplene om hans andre ankomst (Matt 24: 1-36). I den Etiopisk ortodokse tewahedo kirke, den femte søndagen som er halvveis i det store 55 dagers lang fastetiden før etiopiske påske, oppnevnt etter "Debre Zeit". Dagen feires med spesiell oppmerksomhet ifm. Jesus sin gjenkomst, som ble annonsert av vår Herre på Oljeberget. Da han satt på Oljeberget og disiplene var alene med ham, kom de og spurte: «Si oss: Når skal dette skje, og hva er tegnet på ditt komme og verdens ende?» Mens han lærte dem veldig bredt om det andre spørsmålet om tegnene på hans gjenkomst, svarte han kort på det første spørsmålet slikt: "Men den dagen og timen kjenner ingen, ikke englene i himmelen og heller ikke Sønnen, bare Faderen." Matt 24:36

“Metsagu” 4. uken i fastetiden

Den fjerde uken av faste tiden oppnevnt som «Metsagu». Vår kirke lærer i denne uka mye om Herrens makt og helbredelse av de syke. "Metsagu" som betyr pasient eller syk er navnet gitt til mannen som hadde vært syk i trettiåtte år og som hadde ventet på en sjanse til å bli frelst ved den Baptist sjøen, Betesda. Jesus så ham ligge der og visste at han hadde vært syk lenge, og sa til ham: «Vil du bli frisk?» Og Metsagu svarte: «Herre, jeg har ingen som kan få meg ned i dammen. Da sier Jesus til ham: «Stå opp, ta båren din og gå!» Straks ble mannen frisk, og han tok båren sin og gikk. Johannes 5: 1-15

“Mikurab” 3. uken i fastetiden

"Mikurab" betegner "tempel" på norsk. Den 3. uken i hoved fastetiden er oppnevnt etter dette. Tempel er den generelle termen for jødiske bønne- og forsamlingshus. Oppnevnelsen er til minne for at Vår Herre Jesus Kristus lærte folk i tempel og at han gikk i tempelplassen og jaget ut alle dem som drev med noe annet enn Guds bønn.
"Så gikk Jesus inn på tempelplassen og jaget ut alle dem som solgte og kjøpte der. Han veltet pengevekslernes bord og duehandlernes benker og sa til dem: «Det står skrevet: Mitt hus skal kalles et bønnens hus. Men dere gjør det til en røverhule.»" Matt 21፡12-13

Den andre uken i fast tiden “Kidist”

Den andre uken i hoved fast tiden som oppnevnt av komponist, lærer og pioner av den Etiopisk ortodokse tewahedo kirkelige ritualer og sanger, den Hellige Yared, er "Kidist". Det betyr "Hellig". Gud er hellig og han forventer også at vi skal være Hellig. "For det står skrevet: Dere skal være hellige, for jeg er hellig." Peters første brev 1:16.
F.o.m. denne søndagen og hele uken blir det forkynt og sunget om helligheten av sabbaten. Altså lærer vår hellige kirke i denne tiden om hellighet. Første Mosebok 2:3, Andre Mosebok 20:8-11, Tredje Mosebok 19:2-3

Zewerede- den første søndagen av fastetiden

En av de 7 fastetider i den Etiopisk ortodokse kirke heter "Abiy tsom" som betyr hoved fastetid. Årets hoved fastetid begynner mandag 24. februar 2020 og pågår i 55 dager fram til Etiopisk påske. Dette er et eksempel på at Jesus Kristus fastet i førti dager og førti netter rett etter at han ble døpt av døperen Johannes. De 8 ukene i den faste tiden har sin egen merkenavn og betydning. Følgelig kalles den første søndagen og hele uke i fastetiden "Zewerede" som betyr "å stege ned". I den tiden blir det forkynt Guds ord om inkarnasjonen- at Gud kom ned fra himmelen, ble født i Betlehem gjennom Den hellige jomfru Maria og via Den Hellige Ånd til å frelse mennesker. "Ingen annen er steget opp til himmelen enn han som er steget ned fra himmelen: Menneskesønnen, som er i himmelen. Johannes 3:13"

Fastetiden av Nineve

Profeten Jona ble sendt av Gud til folket i Nineve for å omvende seg fra synd. Jona 1-4
I følge av dette ble folket i Ninive vendte til slutt fra sine onde og syndige vei. Da Gud så folket vende om fra sin ondskap, og da han så at de bad om frelse, endret Gud tanken om forbannelsen og det Han hadde tenkt å gjøre med Nineve. Dermed ble byen spart fra ødeleggelse, og alle folkene ble berget!
I den etiopisk ortodokse kirke tro, faster vi til minne av dette og Guds nåde i 3 dager, to uker i forveien av hoved faste tiden før påske. Årets faste av Nineve går f.o.m. 10. februar t.o.m. 12. februar 2020.

Memihir (lærer) Akaleweld Tessema holder preken i vår kirke

Memihir (lærer) Akalewold Tessema, foreleser i filosofi ved den Holy Trinity College i Addis Ababa, er her med oss ​​for å feire dåpen til Jesus Kristos (Timket). Følgelig vil han holde preken om viktige åndelig lære i vår kirke etter Gudstjeneste kommende søndag 26. januar 2020. Menighetsrådet inviterer alle troende til å delta!

 

Årets Timket festival- til minne om Jesu Kristi sin dåp i elven Jordan ble feiret i stor seremoni

Timket festivalen feiret i fellesskap lørdag 19. og søndag 20. januar 2020 i Kristiansand. Dette med tilstedeværelse av De Etiopiske ortodokse tewahedo kirker i Norge. Dvs.
- MAHIDERE SIBEHAT KIDIST LIDETA LEMARIAM KIRKE fra Oslo
- DEN ETIOPISK ORTODOKS TEWAHEDO MEDHANEALEM KIRKE fra Stavanger
- ST. GEORGE DEN ETIOPISK ORTODOKS TEWAHEDO KIRKE fra Trondheim
- MENBERE LEUL ST. MICHAEL ETHIOPISKE ORTODOKSE TEWAHEDO MENIGHET fra Bergen og arrangøren
- DEBRE TSION ST. MARIA ETIOPISK ORTODOKS TEWAHEDO MENIGHET fra Kristiansand. Video klipp

 

Årets feiring av Vår Herre Jesu Kristi sin fødsel

I den Etiopisk ortodokse tewahedo kirke feires fødselen av Vår Herres Jesu Kristi hvert år den 7. januar. Vi feirer årets høytid på kvelden og ut over natten mandag den 06. januar fra kl. 20:00. Det skal arrangeres forskjellige seremonier bl.a. kirkelige ritualer, sanger fra søndagsskolens kor, preken og Gudstjeneste. Menighetsrådet inviterer alle troende velkommen!

Årets høytid av erkeengel Gabriel 28. og 29. desember 2019

Den hellige erkeengel Gabriel er en av de erkeenglene som står ved den himmelske trone og overbringer menneskene åpenbaringer fra Gud. "Jeg er Gabriel, som står for Guds ansikt" (Luk 1:19). I den Etiopisk ortodokse tewahedo kirke feires det 2 årlig høytider til minne for erkeengelen, en i desember og andre i juli. Det som feires nå i desember er til minne for at erkeengelen reddet livet av de tre unge (Hananiah, Azariah og Mishael) som sto fast på deres tro for Gud (Dan 3: 1-30).
Vi feirer høytiden med store arrangement og seremoni fra natt til søndag 28. og 29. desember med kirkelig ritualer, kirke sanger, Gudstjeneste og preken. Alle troende er invitert til å være med!

Økumenisk felles fredsgudstjeneste ifm. utdelingen av Nobels Fredspris

I forbindelse med utdelingen av Nobels Fredspris til Etiopias statsminister Dr. Abiy Ahmed for å ha inngått fred med nabolandet Eritrea og ha fått slutt på en av Afrikas lengst varende og fastlåste konflikter, har den Norges Kristne Råd arrangert økumenisk fredsgudstjeneste i Filadelfiakirken mandag 09. oktober fra kl. 19:00 - 21:00.

Norges Kristne Råd er et fellesskap av forskjellige kristne kirker og trossamfunn. Kristne rådet arrangerer hvert år Gudstjeneste for fredspris vinnere.

Årets seremoni arrangeres ved tilstedeværelse av

  • Erke biskop Abune Elias- fra den etiopisk ortodokse tewahedo kirke
  • Biskop Helga Haugland Byfuglien- fra den norske kirke
  • Generalsekretær Erhard Hermansen- fra Norges Kristne Råde
  • Generalsekretær Dagfinn Høybråten- Kirkens Nødhjelp
  • Etiopisk og Eritreiske kor
  • Ingunn Ulfsten- fra Pinsebevegelsen.

Alle er velkommen til å delta i seremonien. Adresse: Filadelfiakirken , St. Olavs Gate 24, 0166 Oslo.

Det serveres etiopisk kaffe og noe å bite fra kl. 17:30.

Abune Nathaniel

Abune Nathaniel, erkebiskop av East Walega bispedømmet og medlem av Den hellige synode skal være tilstede i vår kirke søndag 13. oktober for å besøke oss og velsigne oss. Menighetsrådet inviterer alle troende velkommen!

Vi har også gleden av å informere at Erhard Hermansen, generell sekretær av Norges Kristne Råd (NKR) kommer på besøk. 

 

Bønn, dåp og helbredende tjeneste

Det er arrangert bønn, dåp og helbredende tjeneste av kesis Mengistu Tilahun from Etiopia f.o.m. mandag 06. mai.
Dette avholdes i vår kirke hverdag fra mandag til lørdag mellom kl. 07:00 og 12:00. Ta kontakt i forkant for mer info.

Innkalling til ordinær generalforsamling

Menighetsrådet innkaller herved medlemmene sine til en ordinær generalforsamling søndag 02. juni 2019 etter Gudstjeneste. Det skal presenteres drift- og regnskapsrapport og diskusjon rundt menighetens framtidige aktivitet. 

Feiring av årets fødselsdag av Vår frue den hellige Jomfru Maria

"Vi gleder oss i dag pga. Vår frue sin fødsel." Fødselsdagen av Vår frue, den hellige Jomfru Maria feires lørdag 11. mai og søndag 12. mai 2019 med tilstedeværelse av Abune Elias, erkebiskop av bispedømmet i Skandinavia i den Etiopisk ortodokse tewahedo kirke og andre inviterte gjester fra både Etiopia og Europa. Menighetsrådet inviterer alle troende velkommen!
"Vår frue den hellige jomfru Maria, din bursdag er vår bursdag!"

Veibeskrivelse til kirken (5 minutter fra Helsfyr stasjon):

  1. Buss nr. 100 fra Helsfyr og ga av på Fjellhus stasjon i 3. stopp.
  2. Buss nr. 66 fra Helsfyr og ga av på Caspar Storms vei i 4. stopp.

 

“Nikodemus” 7. uke i fastetiden

I den Etiopisk ortodokse tewahedo kirke oppnevnt den 7. uken i fastetiden som "Nikodemus", det greske ordet for "seier". Nikodemus var fariseer og en av jødenes rådsherrer. Han var tiltrukket av Vår Herre, men våget ikke å besøke ham åpenlyst. Han pleier å komme til Vår Herre Jesus Kristus om natten og lærer bl.a. om Dåpens sakrament, den Hellige treenighet, mysteriet om inkarnasjonen og Oppstandelsens mysterium. Johannes 3:1-12. Denne uken læres det i vår kirke stort sett om Nikodemus sin personlighet. Nikodemus viste at han var ydmyk, hadde innsikt og var klar over sitt åndelige behov. Han var også modig vitner. Da fariseerne skulle arrestere Vår Herre forsvarte han med å si «Loven vår dømmer vel ikke et menneske uten forhør, før en har fått vite hva det har gjort?» Johannes 7-50-52

Minnestund

Ifm. Dødsfallet av unge Amanuel Tekle og de 157 passasjerer og mannskapet som har mistet livet i flystyrten av Ethiopian airlines flight nr. ET 302, skal det avholdes bønn og minnestund i morgen 17. mars kl. 11:00 etter Gudstjeneste. Adresse: Caspar Storms vei 12, 0664 Oslo, 4. etg. Menighetsrådet.

Den Etiopisk ortodokse Tewahedo kirke Skandinavia bispedømmet avholds første konferanse

Den Etiopisk ortodokse Tewahedo kirke bispedømmet i Skandinavia er en av de 4 bispedømmer i Europa etter restrukturering. Bispedømmet, ledet av erkebiskop Abune Elias, avholdt 2 dagers konferanse 15. og 16. mars 2019 og har vedtatt over viktige saker bl.a. valg av styremedlemmer. Den nye styret består av

  1. Melake amen kesis Lemma Besufekad
  2. Melake berehan Abba G/Giorgis Kassaye
  3. Melake tsiyon Abba Mussie H/Michael
  4. W/ro Rekik Gulilat
  5. Ato Abebe Teferi
  6. Ato Solomon Tefera

 

Feiring av den hellige erkeengl Gabriel sin årlig høytid

I den Etiopisk Ortodokse tewahedo kirke feires det hvert år, 28. desember, minnedag for at den hellige erkeengl Gabriel reddet de 3 unge og trofaste Ananja (Sjadrak), Misael (Mesjak) og Asarja (Abed-Nego) fra ovnen med flammende ild. (Daniel 3:1-30)
Vi feire minnedagen fredag 28. desember fra kl. 07:00 ved vår kirke, Caspar Storms vei 12, 0664 Oslo, med stor arrangement som bl.a. kirkelig ritueller og sanger, Paktens ark seremoni, Gudstjeneste, preken osv. Vi inviterte alle troende til å være med å delta i velsignelsen.

Den hellige erkeengel Gabriel sin årlig høytid ble feiret fredag 28. desember 2018 med forskjellige ulike åndelige arrangementer

Høytiden ble feiret med stor arrangement som bl.a. kirkelig ritualer og sanger, Gudstjeneste, preken osv. Inviterte prester og kirkelig sang vokalist fra Europa og Norge var tilstede og gjør begivenheten til et høydepunkt.

Den Hellige synode har erklært bønn i hele Etiopisk tewahedo kirker og menigheter

Den etiopiske ortodokse tewahedo kirken hellige synode avsluttet sin årlige faste konferanse som ble avholdt mellom 21. og 31. oktober 2018 ved å ha vedtatt 15 punkter sosiale og åndelige avgjørelser for det beste for kirken og landet. Dette bl.a. om situasjonen for tiden i noen deler av Etiopia som er bekymringsfull ift. fred og tolleranse. Og derfor har den hellige synode erklærer bønn i alle Etiopisk tewahedo kirker og menigheter f.o.m. lørdag 10. november t.o.m. 16. november 2018.

Stor kirkelig fellesskap og takksigelse konferanse

Ifm. fred og forsoning som ble gjennomført mellom de 2 hellige synode i Etiopia og i eksil er det arrangert fellesskap og takksigelse konferanse f.o.m. fredag 07. august og t.o.m. søndag 09. august ved den Etiopisk ortodokse tewahedo kirke i Noge, St. Gabriel og hellige Teklehaimanot kirke, Alnafetgata 2, 0192 Oslo.

Alle Medlemmer av den Etiopisk ortodokse tewahedo kirke i Norge er invitert og velkommen til å delta og være med i fellesskap og takksigelse konferansen og bidrar til realisering av pågående endring som består av  budskapsformelen "redusere hat og avsky, multiplisere tilgivelse og forsoning, dele med andre og plusses med kjærlighet og medfølelse".